ምዕራፍ ዘጠኝ#
ስለ ፍርድ ቤቶች አወቃቀርና ሥልጣን#
አንቀጽ 78 ስለ ነጻ የዳኝነት አካል#
ነጻ የዳኝነት አካል በዚህ ሕገ መንግሥት ተቋቁሟል፡፡
የፌዴራሉ መንግሥት ከፍተኛ የዳኝነት አካል የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይሆናል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲደራጅ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ሊወስን ይችላል፡፡ ጉዳዩ በዚህ አኳኊን ካልተወሰነ የፌዴራል ከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ሥልጣን ለክልል ፍርድ ቤቶች ተሰጥቷል፡፡
ክልሎች፣ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች፣ የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶችና የክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች ይኖራቸዋል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይዋሰናል፡፡
የዳኝነት ሥልጣንን ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ወይም በሕግ የመዳኘት ሥልጣን ከተሰጠው ተቋም ውጭ የሚያደርግ፣ በሕግ የተደነገገን የዳኝነት ሥርዓት የማይከተል ልዩ ፍርድ ቤት ወይም ጊዜያዊ ፍርድ ቤት አይቋቋምም፡፡መሰረት የሃይማኖትና የባሕል ፍርድ ቤቶችን ሊያቋቁሙ ወይም እውቅና ሊሰጡ ይችላላላለላሉ፡፡ ይሀ ሕግ መንግሥት ከመጽደቁ በፊት በመንግሥት እውቅና አግኝተው ሲሰራባቸው የነበሩ ሃይማኖቶችና የባሕል ፍርድ ቤቶች በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት እውቅና አግኝተው ይደራጃሉ፡፡
አንቀጽ 79 የዳኝነት ሥልጣን#
በፌዴራልም ሆነ በክልል የዳኝነት ሥልጣን የፍርድ ቤቶች ብቻ ነው፡፡
በየትኛውም ደረጃ የሚገኝ የዳኝነት አካል ከማንኛውም የመንግሥት አካል፣ከማንኛውም ባለሥልጣን ሆነ ከማንኛውም ሌላ ተጽዕኖ ነጻ ነው፡፡
ዳኞች የዳኝነት ተግባራቸውን በሙሉ ነጻነት ያከናውናሉ፡፡ ከሕግ በስተቀር በሌላ ሁኔታ አይመሩም፡፡
ማንኛውም ዳኛ ከዚህ በታች በተመለከቱት ሁኔታዎች ካልሆነ በስተቀር በሕግ ከተወሰነው የጡረታ ዕድሜ ከመድረሱ በፊት ከፈቃዱ ውጭ ከዳኝነት ሥራው አይነሳም፤
ሀ/ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በዳኞች የዲሲኘሊን ሕግ መሠረት ጥፋት ፈጽሟል ወይም ጉልህ የሆነ የሥራ ችሎታና ቅልጥፍና አንሶታል ብሎ ብሎ ሲወስን፣ ወይም
ለ/ በህመም ምክንያት ተግባሩን በተገቢው ሁኔታ ማከናወን አይችልም ብሎ ሲወስን፣ እና
ሐ/ የጉባኤው ውሳኔ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ወይም በክልል ምክር ቤቶች ከግማሽ በላይ ድምጽ ሲጸድቅ፡፡
የማንኛውም ዳኛ የጡረታ መውጫ ጊዜ አይራዘምም፡፡
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት የፌዴራሉን መንግሥት የዳኝነት አካል የሚያስተዳድርበትን በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያስወስናል፣ ሲፈቀድም በጀቱን ያስተዳድራል፡፡
የክልል የዳኝነት አካሎች በጀት በየክልሉ ምክር ቤቶች ይመደባል፡፡ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌዴራሉን የከፍተኛና የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤቶች የዳኝነት ሥልጣን ደርበው ለሚሠሩት የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶችና የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤቶች የበጀት ማካካሻ ይሰጣል፡፡
አንቀጽ 80 የፍርድ ቤቶች ጣምራነትና ሥልጣን#
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል ጉዳዮች ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል፡፡
የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በክልሉ ጉዳይ ላይ የበላይና የመጨረሻ የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ በተጨማሪ የፌዴራል የከፍተኛ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል፡፡
በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ 1 እና 2 የተጠቀሰው ቢኖርም፣
ሀ/ የፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስሕተት ያለበትን ማናቸውንም የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችሎት የማየት ይኖረዋል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡
ለ/ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መሰረታዊ የሆነ የሕግ ስህተት ያለበትንበክልል ጉዳዮች የተሰጠ የመጨረሻ ውሳኔ ለማረም በሰበር ችሎት የማየት ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ ዝርዝሩ በሕግ ይወሰናል፡፡
የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በክልሉ ከሚኖረው የዳኝነት ሥልጣን በተጨማሪየፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣን ይኖረዋል፡፡
የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት የዳኝነት ሥልጣኑ መሰረት በሚሰጠው ውሳኔ ላይ የሚቀርበው ይግባኝ በክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይታያል፡፡
የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት በፌዴራል የዳኝነት ሥልጣኑ በሚሰጠው ውሳኔ ላይየሚቀርበው ይግባኝ በፌዴራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይታያል፡፡
አንቀጽ 81 ስለዳኞች አሿሿም#
የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንትና ምክትል ኘሬዚዳንት በፌዴራልመንግሥት ጠቅላይ ሚኒስትር አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትይሾማሉ፡፡
ሌሎች የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችን በተመለከተ በፌዴራል የዳኞችአስተዳደር ጉባኤ የቀረቡለትን እጩዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቦ ያሾማል፡፡
የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንትና ምክትል ኘሬዚዳንት በክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቅራቢነት በክልሉ ምክር ቤት ይሾማሉ፡፡
የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤትና የክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዳኞች በክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አቅራቢነት በክልሉ ምክር ቤት ይሾማሉ፡፡ የክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ የዳኞችን ሹመት ለምክር ቤቱ ከማቅረቡ በፊት የፌዴራሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ በእጩዎቹ ላይ ያለውን አስተያየት መጠየቅና አስተያየቱን ከራሱ አስተያየት ጋር በማያያዝ ለክልሉ ምክር ቤት የማቅረብ ኃላፊነት አለበት፡፡ የፌዴራሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አስተያየቱን በሦስት ወር ጊዜ ውስጥ ካላቀረበ የክልሉ ምክር ቤት ሹመቱን ያጸድቃል፡፡
የክልል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዳኞች በክልሉ የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ አቅራቢነት በክልሉ ምክር ቤት ይሾማሉ፡፡
በየትኛውም ደረጃ የሚገኙ ዳኞች የዲሲፕሊንና የዝውውር ጉዳይ በሚመለከተው የዳኞች አስተዳደር ጉባኤ ይወሰናል፡፡
አንቀጽ 82 የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አወቃቀር#
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በዚህ ሕገ መንግሥት ተቋቁሟል፡፡
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ አሥራ አንድ አባላት ይኖሩታል፡፡አባላቱም የሚከተሉት ናቸው፣
ሀ/ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ኘሬዚዳንት፣ ሰብሳቢ፤
ለ/ የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ምክትል ኘሬዚዳንት፣ ምክትል ሰብሳቢ፤
ሐ/ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅራቢነት በሪፐብሊኩ ኘሬዚዳንት የሚሾሙ በሙያ ብቃታቸውና በሥነ ምግባራቸው የተመሰከረላቸው ስድስት የሕግ ባለሙያዎች፤
መ/ የፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ከአባላቱ መካከል የሚወክላቸው ሦስት ሰዎች፡፡
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ የሥራ ቅልጥፍናን ለማረጋገጥ የሚያስችለው መዋቅር ሊዘረጋ ይችላል፡፡
አንቀጽ 83 ሕገ መንግሥቱን ስለመተርጐም#
የሕገ መንግሥታዊ ክርክር ጉዳይ ሲነሳ በፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ውሳኔ ያገኛል፡፡
የፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ በሚያቀርብለት ሕገ መንግሥታዊ ጉዳይ ላይ በሠላሣ ቀናት ውስጥ ውሳኔ ይሰጣል፡፡
አንቀጽ 84 የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሥልጣንና ተግባር#
የሕገ መንግሥት ጉዳዮች አጣሪ ጉባኤ ሕገ መንግሥታዊ ጉዳዮችን የማጣራት ሥልጣን ይኖረዋል፡፡ በሚያደርገው ማጣራት መሰረት ሕገ መንግሥቱ መተርጐም አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ የውሳኔ ሐሳብ ያቀርባል፡፡
በፌዴራሉ መንግሥትም ሆነ በክልል ሕግ አውጪ አካላት የሚወጡ ሕጐች ከዚህ ሕገ መንግሥት ጋር ይቃረናሉ የሚል ጥያቄ ሲነሳና ጉዳዩም በሚመለከተው ፍርድ ቤት ወይም በባለ ጉዳዩ ሲቀርብለት መርምሮ ለመጨረሻ ውሳኔ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል፡፡
በፍርድ ቤቶች የሕገ መንግሥት ትርጉም ጥያቄ ሲነሳ፣
ሀ/ ሕገ መንግሥቱን መተርጐም አስፈላጊ ሆኖ ሳያገኘው ሲቀር ጉዳዩን ለሚመለከተው ፍርድ ቤት ይመልሳል፤ በአጣሪ ጉባኤው ውሳኔ ቅር የተሰኘ ባለጉዳይ ቅሬታውን ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት በይግባኝ ማቅረብ ይችላል፡፡
ለ/ የትርጉም ጥያቄ መኖሩን ያመነበት እንደሆነ በጉዳዩ ላይ የሚሰጠውን ሕገ መንግሥታዊ ትርጉም ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ለመጨረሻ ውሳኔ ያቀርባል፡፡ የሚመራበትን ሥነ ሥርዓት አርቅቆ ለፌዴሬሽኑ ምክር ቤት ያቀርባል፣ ሲፈቀድም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡