ምዕራፍ አሥር#

የብሔራዊ ፖሊሲ መርሆዎችና ዓላማዎች#

አንቀጽ 85 ዓላማዎች#

  1. ማንኛውም የመንግሥት አካል ሕገ መንግሥቱን፣ ሌሎች ሕጐችንና ፖሊሲዎችን ሥራ ላይ ሲያውል በዚህ ምዕራፍ በተመለከቱት መርሆዎችና ዓላማዎች ላይ መመስረት አለበት፡፡

  2. በዚህ ምዕራፍ ውስጥ «መንግሥት» ማለት እንደየሁኔታው የፌዴራል መንግሥት ወይም የክልል መስተዳድሮች ማለት ይሆናል፡፡

አንቀጽ 86 የውጭ ግንኙነት መርሆዎች#

  1. የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጥቅም የሚያስጠብቅና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት የሚያስከብር የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ ማራመድ፡፡

  2. የመንግሥታትን ሉዓላዊነትና እኩልነት ማክበር፣ በሌሎች ሀገሮች ጉዳዮች ውስጥ ጣልቃ አለመግባት፡፡

  3. የሀገሪቱ የውጭ ግንኙነት ፖሊሲ በጋራ ጥቅምና በእኩልነት ላይ የተመሰረተ መሆኑን እንዲሁም በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ ስምምነቶች የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከብሩ መሆናቸውን ማረጋገጥ፡፡

  4. የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚያስከብሩና የሕዝቦኟን ጥቅም የማይጻረሩ ዓለም አቀፍ ሕጐችና ስምምነቶችን ማክበር፡፡

  5. ከጐረቤት ሀገሮችና ከሌሎችም የአፍሪካ ሀገሮች ጋር በየጊዜው እያደገ የሚሄድ ኢኮኖሚያዊ ኅብረትና የሕዝቦች ወንድማማችነትን ማጐልበት፡፡

  6. በሀገሮች መካከል የሚነሱ ግጭቶች ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈቱ ጥረት ማድረግ፡፡

አንቀጽ 87 የመከላከያ መርሆዎች#

  1. የሀገሪቱ የመከላከያ ሠራዊት የብሔሮች፣ የብሔረሰቦች እና የሕዝቦችን ሚዛናዊ ተዋጽኦ ያካተተ ይሆናል፡፡

  2. የመከላከያ ሚኒስትር ሆኖ የሚሾመው ሲቪል ይሆናል፡፡

  3. የመከላከያ ሠራዊት የሀገሪቱን ሉዓላዊነት ከመጠበቅ በተጨማሪ በዚህ ሕገ መንግሥት መሰረት በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የሚሰጡትን ተግባሮች ያከናውናል፡፡

  4. የመከላከያ ሠራዊቱ በማናቸውም ጊዜ ለሕገ መንግሥቱ ተገዢ ይሆናል፡፡

  5. የመከላከያ ሠራዊቱ ተግባሩን ከፖለቲካ ድርጅቶች ወገናዊነት ነጻ በሆነ አኳኊን ያከናውናል፡፡

አንቀጽ 88 ፖለቲካ ነክ ዓላማዎች#

  1. መንግሥት በዴሞክራሲያዊ መርሆዎች ላይ በመመሥረት ሕዝቡ በሁሉም ደረጃዎች ራሱን በራሱ የሚያስተዳድርበትን ሁኔታ ማመቻቸት አለበት፡

  2. መንግሥት የብሔሮችን፣ የብሔረሰቦችን፣ የሕዝቦችን ማንነት የማክበርና በዚሁ ላይ በመመርኮዝ በመካከላቸው እኩልነት፣ አንድነትና ወንድማማችነትን የማጠናከር ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ 89 ኢኮኖሚ ነክ ዓላማዎች#

  1. መንግሥት ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሀገሪቱ የተጠራቀመ እውቀትና ሀብት ተጠ ቃሚዎች የሚሆኑበትን መንገድ የመቀየስ ኃላፊነት አለበት፡፡

  2. መንግሥት የኢትዮጵያውያንን የኢኮኖሚ ሁኔታዎች ለማሻሻል እኩል ዕድል እንዲኖራቸው ለማድረግና ሀብት ፍትሐዊ በሆነ መንገድ የሚከፋፈሉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ግዴታ አለበት፡፡

  3. የተፈጥሮና ሰው ሰራሽ አደጋ እንዳይደርስ መከላከልና አደጋው ሲደርስም ለተጐጂው እርዳታ በወቅቱ እንዲደርስ ማድረግ፡፡

  4. በእድገት ወደኊላ ለቀሩ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦች፣ ሕዝቦች መንግሥት ልዩ ድጋፍ ያደርጋል፡፡

  5. መንግሥት መሬትንና የተፈጥሮ ሀብትን በሕዝብ ሥም በይዞታው ሥር በማድረግ ለሕዝቡ የጋራ ጥቅምና እድገት እንዲውሉ የማድረግ ኃላፊነት አለበት፡፡

  6. የሀገር ልማት ፖሊሲዎችና ኘሮግራሞች በሚዘጋጁበት ወቅት መንግሥት ሕዝቡን በየደረጃው ማሳተፍ አለበት፡፡ የሕዝብንም የልማት እንቅስቃሴዎች መደገፍ አለበት፡፡

  7. መንግሥት በሀገር ኢኮኖሚያዊና ማኅበራዊ ልማት እንቅስቃሴ ውስጥ ሴቶች ከወንዶች ጋር በእኩልነት የሚሳተፉበትን ሁኔታ የማመቻቸት ኃላፊነት አለበት፡፡

  8. መንግሥት የሠራተኛውን ሕዝብ ጤንነት፣ ደህንነትና የኑሮ ደረጃ ለመጠበቅ መጣር አለበት፡፡

አንቀጽ 90 ማኅበራዊ ነክ ዓላማዎች#

  1. የሀየሀገሪቱ አቅም በፈቀደ መጠን ሁሉም ኢትዮጵያዊ የትምህርት፣ የጤና አገልግሎት፣ የንoህ ውሃ፣ የመኖሪያ፣ የምግብና የማኅበራዊ ዋስትና እንዲኖረው ይደረጋል፡፡

  2. ትምህርት በማናቸውም ረገድ ከሃይማኖት፣ ከፖለቲካ አመለካከቶች እና ከባህላዊ ተፅእኖዎች ነጻ በሆነ መንገድ መካሔድ አለበት፡፡

አንቀጽ 91 ባሕል ነክ ዓላማዎች#

  1. መንግሥት መሰረታዊ መብቶችንና ሰብዓዊ ክብርን፣ ዴሞክራሲንና ሕገ መንግሥቱን የማይቃረኑ ባሕሎችና ልማዶች በእኩልነት እንዲጐለብቱና እንዲያድጉ የመርዳት ኃላፊነት አለበት፡፡

  2. የሀገር የተፈጥሮ ሀብቶችንና የታሪክ ቅርሶችን መጠበቅ የመንግሥትና የሁሉም ኢትዮጵያዊ ግዴታ ነው፡፡

  3. መንግሥት አቅም በፈቀደ መጠን ኪነጥበብን፣ ሳይንስንና ቴኖሎጂን የማስፋፋት ግዴታ አለበት፡፡

አንቀጽ 92 የአካባቢ ደህንነት ጥበቃ ዓላማዎች#

  1. መንግሥት ሁሉም ኢትዮጵያዊ ንoሕና ጤናማ አካባቢ እንዲኖረው የመጣር ኃላፊነት አለበት፡፡

  2. ማንኛውም የኢኮኖሚ ልማት እርምጃ የአካባቢውን ደህንነት የሚያናጋ መሆን አለበት፡፡

  3. የሕዝብን የአካባቢ ደህንነት የሚመለከት ፖሊሲና ኘሮግራም በሚነደፍበትና ሥራ ላይ በሚውልበት ጊዜ የሚመለከተው ሕዝብ ሁሉ ሐሳቡን እንዲገልጽ መደረግ አለበት፡፡

  4. መንግሥትና ዜጐች አካባቢያቸውን የመንከባከብ ግዴታ አለባቸው፡፡