, , , ,

የትግራይ ህዝብ እና የህውሓት ግኑኝነት ነባራዊ ገፅታ

ማሕበር ረድኤት ትግራይ /ማረት/REST/

ይህ ድርጅት ላይ ላዩን በእርዳታና በልማት ስራ የተሰማራ ሲቪክ ተቋም ይምሰል እንጂ በብዙዎች ዘንድ ያልተባነነበት mighty የፖለቲካ ድርጅት ነው። በክልሉ ከፍተኛ የፖለቲካ ስልጣን ያለውና ህዝቡን በቁጥጥራቸው ስር ለማድረግ የሚጠቀሙበት ቁጥር አንድ የፖለቲካ መሳሪያቸው ነው። የመሳሪያዎቹ ዝርዝር ከቀላል ወደ ከባድ፥

1• ማረት በህዝብ ስም እርዳታ ይጠይቃል። እርዳታ የፖለቲካ መሳሪያ ነው። የህውሓትን ትዕዛዝ የማያከብር ድሃ በእርዳታ ይቀጣል። ከምግብ ለስራ ይሰናበታል። ወዘተ። ድሃን በጉሮሮው ከቀጣኸው ጉልበት ኖሮት ሊቃወምህ አይችልም። ስለዚህ ቀዳሚው የህውሓት ስራ አብዛኛውን የህዝብ ክፍል አደህይቶ የመግዛት ፖሊሲውን ማስቀጠል መቻሉ ነው። በቁጥጥሩ ስር በሆነ የማረት ተቋም እርዳታና የምግብ ለስራ እድሎችን በመስጠትና በመንፈግ በቀላሉ ህዝቡን ለማንበርከክ የተዋጣለት ከፖሊሲው ጋር የተቀናጀ የፖለቲካ መሳሪያ ሆኖ አገልግሎታል።

2• ህውሓት ማንኛውም ዓይነት የውጭ ግብረሰናይ ድርጅት (NGO) ትግራይ ውስጥ ራሱን ችሎ እንዳይንቀሳቀስ ገና ጫካ እያለ ጀምሮ በህግ አግዷል። ፕሮጀክታቸውንና ገንዘባቸውን ይዘው መጥተው ለማረት በማስረከብ፣ በማረት አማካኝነት ፕሮጀክቱ ተፈጻሚ እንዲሆን የሚጠይቅ አሰራር ይከተላል። መያዶቹ ከተስማሙ የፕሮጀክቱን ሂደት አልፎ አልፎ ሱፐርቫይዝ ለማድረግ ብቻ ይፈቀድላቸዋል። ካልተስማሙ ገንዛባቸውንና ፕሮጀክታቸውን ይዘው ወደ መጡበት እንዲመለሱ ያደረጋል። ህዝቡ መሃል ገብተው በራሳቸው እቅድና የአፈጻጸም መንገድ እንዲሰሩ ህውሓት ፈጽሞ አይፈቅድላቸውም፤ በሁለት ዋና ዋና ምክንያቶች፥ የመጀመሪያው የውጪ ድርጅቶች ህዝቡን ቀርበው በማነጋገር ህዝቡ ያለበትን ትክክለኛ ሁኔታ እንዳያወቅ፣ አውቀውም ወደ ውጪ እንዳይወጡት በመፈለግ ሲሆን ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከህውሓት ቁጥጥር ውጪ የሆነ ገቢ ህዝቡ እንዲኖረው ስለማይፈለግ ነው።

እነዚህ ሁለቱ ምክንያቶች ህውሓት በክልሉ የሚኖረውን ሃይል ማዳከም የሚችሉ መሆናቸውን ልብ ይሏል። ዛሬ NGOዎች ስፖንሰር ያደረጉትን ፕሮጀክት ሱፐርቫይዝ ሲያደርጉ የሚያነጋግሩት ህውሓት ያዘጋጀላቸውን ካድሬዎችን ብቻ ነው። ህውሓት ያላዘጋጃቸው በዕጣ የተመረጡ ተራ ሰዎች ስለሚኖሩበት ህይወት በትክክል እንዲናገሩ አይደረግም። ድንገት ተመርጠው ከሆነም ካድሬ በመሃከላቸው እንዲገኝ ተደርጎ ስለሚናገሩት ነገር እየተሰለሉ ነው። በተናገሩት መሰረት ከተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞች እንዲገለሉ እንደሚደረጉ ስለሚያውቁ ያሉበትን ሁኔታ በትክክል ለመናገር ይፈራሉ። በዚህ ምክንያት በተለይ ለውጭ ሚድያዎችና የሰብአዊ መብት ድርጅቶች ክልሉ ዝግ እንደሆነ እስከዛሬ ድረስ አለ። በሌላ በኩል ደግሞ ከህውሓት ቁጥጥር ውጪ የሆነ ገቢ የሚያገኝ ሰው፣ በህውሓት መታዘዝን አሻፈረኝ ሊል ይችላልና ለፖለቲካ ህልውናቸው አደጋ ነው። ስለሆነም ህውሓቶች ይህን ሊፈቅዱ ፈጽሞ አይችሉም።

3• ማረት ከእርዳታ ውጪ በ”ልማት” ትርፍ በሚያስገኙ የንግድ ስራዎች ላይ የተሰማራ ድርጅት ነው። “የልማት” ስራው ባብዛኛው ፕሮጀክቶችን ቀርጾ በፕሮጀክት ስም ከውጪ ለሚያገኘው ገንዘብ እንደ ሽፋን የሚጠቀምበት የማጨናበሪያ መንገድ ሲሆን፣ ጎን ለጎን ደግሞ የማሳያውን ልማትም ቢሆን የሚሰራው ለድርጅቱ ታዛዥ የሆኑ አካባቢዎችንና ግለሰቦችን ታርጌት ባደረገ መልኩ ነው። ያም ሆኖ አንዱን የልማት ስራ ከሶስት ወይም አራት የተላያዩ ፕሮጀክቶች ሂሳብ እያወራረደ ኪሱን የሚሞላበት አሰራርን ዘርግቷል። በዚህ መንገድ የሚገኘው ትርፍ የህውሓትን ኪስ ከማደለብ ባሻገር ህዝቡን በሚከተለው መንገድ ለማፈን ይጠቀሙበታል።

4•  ማረት የብድር ሰጪ ተቋም (ደደቢት) በውስጥ ስላለው በዚህ ተቋም አማካኝነት በተለይ ድሃው ገበሬ በተለያዩ ምክንያቶች ብድር እንዲወስድ በህውሓት ይገደዳል። የብድሩ ምንጭ የማረት ትርፍ ነው። የማረት ትርፍ የሚመጣው በተጨናበረ መንገድ ነው። ገበሬው ያለፈቃዱና ያለ በቂ ስልጠና ተገድዶ ለማዳበሪያ ለምርጥ ዘርና ለመሳሰሉ የምርት ግብዓቶች እንዲህውም መጤ የግብርና ፓኬጆች ብድር እንዲወስድ ይደረጋል። ማዳበሪያና ምርጥ ዘር እንዲህውም ሌሎች ግብዓቶችን የሚያቀርበው ጉና ነው። ጉና በEFFORT ስር ነው። ጉና ምርቱን ለገበሬ አስገድዶ በመሸጥ ያተርፋል። ገበሬው በራሱ ጥሬ ገንዘብ መግዛት ስለማይችል፥ ብድር ከማረት በከፍተኛ ወለድ እንዲወስድ ይደረጋል። ማረት ሌላ ትርፍ ያጋብሳል። ገበሬው ብድሩን ለመክፈል ፍዳውን ያያል። ብድሩን ለመክፈል የግድ በእርዳታና በምግብ ለስራ ፕሮጀክቶች ስር መታቀፍ መቻል ይኖርበታል። በነዚህ ስር ታቅፎ ተጠቃሚ ለመሆን ደግሞ፣ ለህውሓት ታዛዥነቱንና አሜን ባይነቱን ማረጋገጥ አለበት። ወዘተ።

በዚህ ሁኔታ ነው ገበሬውን ሸብበው የያዙት። በተለይ ትግራይ ውስጥ 85 በመቶ የሚሆነው ህዝብ (ገበሬው) በኛ ቁጥጥር ስር ነው ሲሉ ደጋግመው የሚፎልሉትም በዚህ ምክንያት ነው። ገበሬው መቼም ቢሆን አንገቱን ቀና ማድረግ እንዳይችል የተወሳሰበ አሰራር ዘርግተው አስረውታል። ዛሬ የጎንደር ምሊሻ ገበሬና የኦሮሚያ ገበሬ ለነጻነቱ እንደቆመው ዓይነት ተቃውሞ ከትግራይ ገበሬው ይነሳባቸዋል ብሎ ማሰብ ይከብዳል። ገበሬው ካልተነሳ ደግሞ ሌላው ያን ያክል ስጋት ላይ የሚጥላቸው ባይሆንም ለሱም የሚቀጥለውን መሸበቢያ አሰራር ዘርግተዋል።

5 replies
  1. Simon
    Simon says:

    እጅግ በጣም ገራሚ ትንተና ነዉ ሶሎሞን ያቀረብከዉ!!! እዉነታዉን ከነ ሙሉ ጭብጦቹ ስላቀረብከዉ በጣም ልትመሰገን ይገባል!!!

    Reply
  2. kedir Seid Mohammed
    kedir Seid Mohammed says:

    እንደኔ እምነት ይህ ጽሁፍ የትግራይ ህዝብ ያለበትን ተጨባጭ በጥልቀት የመረመረ፤ ምናልባትም ስለ ትግራይና ስለ ህዝቧ አስመልክቶ እስካሁን ካነበብናቸው ጽሁፎች በይዘትም በአቀራረብም የተለየ እንደሆነ አምናለው እናም ካለው ነባራዊ ሁኔታ ተነስቼም እውነት የትግራይ ህዝብ ምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው፤ ከሌላው ማህበረሰብ ለየት ያለ የስርአቱ ታማኝ ደጋፊ እንዲሆን ያስቻለው፤ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛላቸው ያደረገው እውነት ወዶ በፍቃዱ ነው ወይስ ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን አይነት ነገር ሆኖበት ነው እናም የመሳሰሉ የብዙ ሰዎች ጥያቄ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ መልስ እንደሚገኝባቸው አምናለው። ምናልባትም ያለንን የተሳሳተ እይታ ያስተካክላል ብየ ተስፋ አደርጋለው። ብዙዎቻችን ያለን አመለካከት ላይ ላይ ከሚታዩት አንድአንድ ማኒፈስቴሽኖች የዘለለ በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ያለን መስሎ አይሰማኝም።

    መልካም ንባብ ፡)

    Reply

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *