, , , ,

የትግራይ ህዝብ እና የህውሓት ግኑኝነት ነባራዊ ገፅታ

ማጠቃለያ

ፕ/ር መስፍን እና ሌሎችም ከዚህ በፊት እንዳሉት የመጨረሻው የድህነት ወለል ላይ ያሉት፣ ቤት ንብረታቸውን ጥለው በአዲስአበባና ሌሎች ከተማዎች ጎዳና ላይ ሲለምኑ የሚውሉ የኔ ቢጤዎች በብዛት ከትግራይ የተሰደዱ ናቸው። ይህ ብቻ አይደለም፣ የሚላስ የሚቀመስ የሌለው፣ የህውሓትን ይሁንታና ምጽዋት ሲጠባበቅ የሚኖረው ህዝብ በትግራይ ያለ ማጋነን ከ80 በመቶ በላይ ይሆናል። ምጽዋት የማይጠብቁ የሚባሉት የመንግስት ሰራተኞች ራሱ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ ከእጅ ወደ አፍ የሆነ ኑሮ ሲኖሩ ይታያሉ። በተዘረጋባቸው የፖለቲካ መሳሪያ አማካኝነት ታፍነው ይኖራሉ። ብሶታቸውን ለመግለጽ ይፈራሉ። እንደምንም ወደ ውጭ ቢወጡ እንኳን፣ ከወጡ ብኋላም ፍርሃቱ አይለቃቸውም። ህውሓትን ይፈራሉ፣ በዘራቸው ምክንያት እንዳያጠቃቸው ሌላውን ይፈራሉ። የአጣብቂኝ ህይወት ውስጥ ይኖራሉ።

በእርግጥ በዛው ልክ ደግሞ ከህውሓት ጋር አሸሸ ገዳሜ የሚሉ፣ በህዝብ ስም የሚነግዱ፣ በህዝብ ስም ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር የሚጋጩ፣ በሌላው ሀዘን ላይ የሚጨፍሩ፣ በሌላው ደስታ ላይ ማቅ የሚለብሱ፣ ሆን ብለው ህዝቡ በሌላ እንዲጠላ የሚሰሩ የህውሓት ገረዶች አሉ። ህውሓት የሚፈልገው ስለሆነ ያሰማራቸው ካድሬዎች ናቸው። በተጠና መንገድ ተግባራዊ እየሆነ ያለ፣ ትግራይንና ትግራዋይን ከሌላው የመነጠል ስራ ነው።

የፖለቲካና የኢኮኖሚ የበላይነታቸውን በኢትዮጵያ ማስጠበቅ ካልቻሉ፣ ቢያንስ በትግራይ ማስጠበቅ ይኖርብናል ብለው ያስባሉ። ምሽጋቸውን ትግራይ ላይ እየቆፈሩ ነው። ትግራይን ቄጤማ አድርገዋታልና በከፋ ቀን ጉዝጓዛቸው ትሆን ዘንድ በዝግጅት ላይ ነች። የዚህ እንድምታ ለብዙዎቻችን ምናልባት በደንብ አልገባን ይሆን ይሆናል። ምናልባት ሊታወቅ የማይችል ሊሆን ይችላል። ዛሬ ደርሰው የዓፈርንና የሶማሌን ብሄርተኝነት የሚያራግቡት፡ የተቀረውን ኢትዮጵያዊ በዘር ከፋፍለው በማበጣበጥ እነሱ በትግራይ ለመሸሸግ ይመስላል። ምናልባት ሌላው ሲባላ እነሱ ደልቷቸው የሚኖሩ መስሏቸው ሊሆን ይችላል። ፍላጎታቸው ምንም ይሁን ምን ትግራይንና ኢትዮጵያን ከዚህ ድርጅትና ከነዚህ ሰዎች ማስጣል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀላፊነትና ግዴታ ሊሆን ይገባል።

በሌላው ክልል እንደምናዬው በአጭር ጊዜ ውስጥ በራሱ ተነሳሽነት የትግራይ ህዝብ በተቃውሞ ይነሳል የሚለው እምነቴ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሸረሸረ መጥቷል። ምክንያቱም ህዝቡ ህውሓትን ይፈራል፣ ሌላውን ወገኑንም ይፈራል። በተቃውሞ ለመነሳት አንዳቸውን መፍራት የግድ ማቆም አለበት። ሌላውን ወገኑን መፍራት እንዲያቆም በሌላው ወገኑ በኩል የአወንታ ምልክቶችና የትግል አጋርነቶችን ማየት አለበት። ህዝቡን ማግለልና ከህውሓት ጋር ደርቦ መፈረጅ ስህተት ስለሆነ ሊታረም ይገባል። ይህ ካልሆነ ግን ሌላውን ወገኑን እየፈራ ህውሓትን ሳይፈራ ለመታገል ይከብደዋል። ምክንያቱም ሌላውን እየፈራ ህውሓትን ሳይፈራ ጭቆና በቃኝ ብሎ ለመነሳት፣ ጠንካራ ትግራዋይነትን (ትግራዋይ ድርጅትን) መፍጠር ይጠበቅበታል። ከህውሓት ብኋላ ህልውናውን ለማስጠበቅ በደንብ መደራጀት እንደሚኖርበት የግድ ማመን ካለበት፣ ያንን ለማሳካት ጊዜ ይፈጃልና በቅርቡ ተቃውሞ ሊያስነሳ አይችልም። ከጊዜው አንጻር የተሻለው አማራጭ ትግራይንም ያካተተ፣ ትግራይን ከህውሓት ነጻ ለመውጣት ጭምር ያለመ ኢትዮጵያዊ ትግል ማካሄድ ነው። ይህን ማድረግ ግድ ይላል።ህውሓት እንደ ድርጅት እስካለ ድረስ የትኛውም የኢትዮጵያ ክፍል በሰላም ሊኖር አይችልምና ህውሓት ከኢትዮጵያ ምድር እስከወዲያኛው ማስወገድ ብቸኛው የማታገያ መንገድ ሊሆን ይገባል።

በመጨረሻ በተለይ ህዝባችን ያለበት ሁኔታ የሚያሳስበን በውጪ የምንኖር የትግራይ ተወላጆች ከሌሎች ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችን ጋር በመተባበር በህውሓት ምክንያት ዜጎች እየደረሰባቸውን ያለ ግፍ በጋር በማውገዘ የትግል አጋርነታችንን በግልፅ ማሳየት አለብን። በትግራይ ያለዉን እውነተኛ ገፅታ ለሌላው ኢትዮጵያዊ ማስረዳት ይጠበቅብናል። የትግራይ ህዝብም ለነፃነቱ እንደማንኛውም ኢትዮጵያዊ እንዲቆም ማነሳሳት ይጠበቅብናል። በቃኝ የሚልበትን ጊዜ ለማፋጠን ብዙ መስራት ይጠበቅብናል። በፕ/ር መስፍን የቀረበ የመፍትሔ ሀሳብ በማካፈል ፅሁፌን ላጠናቅቅ።

5 replies
  1. Simon
    Simon says:

    እጅግ በጣም ገራሚ ትንተና ነዉ ሶሎሞን ያቀረብከዉ!!! እዉነታዉን ከነ ሙሉ ጭብጦቹ ስላቀረብከዉ በጣም ልትመሰገን ይገባል!!!

    Reply
  2. kedir Seid Mohammed
    kedir Seid Mohammed says:

    እንደኔ እምነት ይህ ጽሁፍ የትግራይ ህዝብ ያለበትን ተጨባጭ በጥልቀት የመረመረ፤ ምናልባትም ስለ ትግራይና ስለ ህዝቧ አስመልክቶ እስካሁን ካነበብናቸው ጽሁፎች በይዘትም በአቀራረብም የተለየ እንደሆነ አምናለው እናም ካለው ነባራዊ ሁኔታ ተነስቼም እውነት የትግራይ ህዝብ ምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው፤ ከሌላው ማህበረሰብ ለየት ያለ የስርአቱ ታማኝ ደጋፊ እንዲሆን ያስቻለው፤ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛላቸው ያደረገው እውነት ወዶ በፍቃዱ ነው ወይስ ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን አይነት ነገር ሆኖበት ነው እናም የመሳሰሉ የብዙ ሰዎች ጥያቄ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ መልስ እንደሚገኝባቸው አምናለው። ምናልባትም ያለንን የተሳሳተ እይታ ያስተካክላል ብየ ተስፋ አደርጋለው። ብዙዎቻችን ያለን አመለካከት ላይ ላይ ከሚታዩት አንድአንድ ማኒፈስቴሽኖች የዘለለ በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ያለን መስሎ አይሰማኝም።

    መልካም ንባብ ፡)

    Reply

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *