የኢሬቻ እልቂት – IrreechaMassacre

IrreechaMassacre – ትላንትና እሁድ (02.10.2016 እኤአ) ከተለያዩ ቦታዎች የመጡ ወገኖቻችን  በተገኙበትና በቢሾፍቱ እየተካሄደ በነበረ የኦሮሞ ባህል የሆነው የኢሬቻ ክብረ በዓል ላይ “የመንግስት” (የወንበዴው!) ታጣቂዎች በዜጎች ላይ በከፈቱት ተኩስ ከ500 ሰዎች በላይ ለህልፈት መዳረጋቸው ይታወቃል።

ይህን ተከትሎ በተለያዩ ቦታዎች በተነሳ ህዝባዊ እንቢተኝነት የወንበዴው  ታጣቂዎች አሁንም ተኩስ ከፍተው የሰው ህይወት እየቀጠፉ ይገኛሉ። ይህ እልቂት ኢትዮጵያውያን እስከዛሬ ድረስ በታሪካችን አይተነውና ሰምተነው የማናውቅ አሰቃቂ እልቂት ሲሆን፥ በላያችን ላይ የተፈፀመው በባዕድ ሳይሆን ከራሳችን በወጡ አውሬዎች መሆኑ ደግሞ እጅግ ልብን የሚያደማና ቅስምን የሚሰብር ነው። ያለሁበትን ሁኔታ ለመግለፅ ቃላቶች ያጥሩኛል፥ መገመት ከምትችሉት በላይ አዝኛለሁ። ስራ መስራት አልቻልኩም። በበኩሌ እንደ አንድ ተራ ግለሰብ ማድረግ የምችለው ይህን ነውና፥ ለምን ተናግሬው አይወጣልኝም በማለት ይህን ቪድዮ  አዘጋጀሁ። ለተጠቀምኩባቸው ቃላት ይቅርታ! እልቂቱ ያሳብዳል እንኳንና ይህን ለመናገር!

0 replies

Leave a Reply

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *