አራቱ የኢትዮጵያ ህገ-መንግስታት
አራቱ የኢትዮጵያ ህገ-መንግስታት December 26, 2023 በአብዛኛዉ የታሪክ ክፍል የኢትዮጵያ አስተዳደር በሁለት ቁልፍ ሰነዶች ይመራ ነበር፡ በክብረ ነገስት እና በፍትሀ ነገስት። በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጻፈው ክብረ ነገስት፣ የስልጣን ምንጭ…
አራቱ የኢትዮጵያ ህገ-መንግስታት December 26, 2023 በአብዛኛዉ የታሪክ ክፍል የኢትዮጵያ አስተዳደር በሁለት ቁልፍ ሰነዶች ይመራ ነበር፡ በክብረ ነገስት እና በፍትሀ ነገስት። በ14ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የተጻፈው ክብረ ነገስት፣ የስልጣን ምንጭ…
የአሰብ ወደብ ጦርነት አይቀሬ ነው። ሁለቱም አገራት እየተዘጋጁበት እንዳሉ መረጃዎች እየወጡ ነው። በኤርትራውያን ዘንድ ኢትዮጵያ ጦሯን ድንበር ላይ እያሰማራች ነው፣ የአለም ትኩረት ጋዛ ላይ ባለበት በኣሁኑ ወቅት ድንገት ጥቃት ልትከፍት ትችላለች የሚል ከፍተኛ ስጋት አለ። ጦርነቱ ከተጀመረ፣ ህልማቸው መና እንደሚቀርና ታሪክ ሆነው እንደሚቀሩ ስለገባቸው፣ ኤርትራውያን አረቦቹንም እነ ቻይናንም አሸማግሉን የሚል ተማጽኖ እያሰሙ ነው። በሌላ በኩል ደግሞ ህልማቸው የቀጠናው ቁንጮ መሆን ነውና፣ ይህን ለማሳከት ኢትዮጵያን እንደፈለጉት መጠምዘዝ ባይችሉ፣ እንድትበጣበጥና እንድትበተን ሳይታክቱ ከመስራት አይቆጠቡም። ለዚህም ፋኖን በዋናነት እየተጠቀሙበት ይገኛሉ።
የአብይ መንግስት አሁን ባለበት ሁኔት፣ ከጦርነት አዙሪት የመውጣት እድሉ ዝቅተኛ እንደሆነ ተገንዝቧል። በዚች አጭር የስልጣን ዘመኑ፣ ከማንምና ከምንም በላይ ለስልጣኑ ሲል በህዝቦች መካከል ያለውን ቅራኔ በማስፋቱ፣ ከጦርነት አዙሪት ሊወጣ አይችልም። ከኣንዱ ጋር በድርድርም ሆነ በሌላ መንገድ ሰላም ቢያወርድ፣ አውቶማቲካሊ ከሌላው ጋር ጦርነት ይጀምራል፤ ቅራኔያቸውን በመስፋቱ ስጋት እንጂ መተማመን የላቸውም። ከዚህ አዙሪት ለመውጣት ድሮ ያመለጠውን ዕድል፣ ማለትም ህዝቦችን የማወያየትና የማቀራረብ ስራ ልስራ ቢል እንኳን፣ የኤርትራ ጣልቃ ገብነትና ፍትፈታ እስካለ ድረስ አይሳካለትም። ስለሆነም ቀዳሚ ታርጌቱ ኤርትራ ትሆናለች። የወደብ ጦርነቱን አይቀሬ የሚያደርገው ደግሞ ይኸው ነው።
የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ በስተቀር፣ ኢትዮጵያ እንደአገር ከቀጠለች አሰብ ወደ ኢትዮጵያ መመለሷ አይቀሬ ነው። የማይቀርለት ጉዳይ ዛሬ በመድፈርና አሰብን በማስመለስ፣ በሁሉም ዘንድ ተቀባይነትን ያጣው የአብይ መንግስት፣ በተወሰነ ደረጃ ተቀባይነትን እንዲያገኝ ይረዳዋል። ከምንም በላይ ደግሞ የህዝቡን ትኩረት ከአገር ውስጥ ወደ ውጭ በማስቀየስ፣ ድጋፍ የማግኘት እድሉን ይጨምርለታል። ጦርነቱ ከተጀመረ የማሸነፍ እድሉ ከፍተኛ እንደሆነ ያቃል። አሸንፎ በኢትዮጵያ ጉዳይ የሚፈተፍቱ የሻዕቢያ እጆችን ከቆረጠ፣ የአገር ውስጥ ተቀናቃኞቹ (በተለይ የአማራ ሸኔ የሚላቸው) ገመዳቸው አጠረ ኦክስጅናቸው ተበጠሰ ማለት ነው። እነሱንም የማንበርከክ አቅሙ ይጎለብታል።
ይህ ከሆነ፣ ስልጣኑን አራዘመ ማለት ነው። ከጦርነት አዙሪት የመውጣት እድሉም ይኖረዋል። ሻዕቢያን አጥፍቶ፣ አሰብን አስመልሶ፣ በሻዕቢያ የሚታገዙ የአገር ውስጥ ተቀናቃኞቹን ካኮላሸ፣ ወደ ልማትና ህዝብን የማቀራረብ ስራ በመመለስ፣ አገሪቱ ከጦርነት አዙሪት የምትወጣበትን መንገድ መፍጠር ይችላል ማለት ነው። ለዚህም ነው ሊያከትምለት አንድ ሓሙስ በቀረው በአሁን ወቅት የአሰብ ካርድ ደምቃ የታየችው።
ይችን ካርድ ባይስባትስ? አሸናፊ በሌለው የእርስ በእርስ ግጭት እንደሚዳክር ያውቃል። በመጨረሻም እጣፈንታው ከፍ ቢል እንደ ሶሪያ (የመንደር ንጉስ መሆን) አሊያም እንደነ ሊብያ ከስሞ የጎስት አገር መፍጠር እንደሚሆን ያውቃል።
እናም አጅሬ ተዘጋጅቷል፣ እናንተም ለባሰ የኑሮ ውድነት ተዘጋጁ። (እንደወረደ!)
ከህዝብ እይታ ለበርካታ ሳምንታት ርቀው የቆዩት ዶ/ር አብይ አሕመድ አሊ፣ ትላንትና ማታ በአንድ የአውሮፕላን አምቡላንስ ከአዲስ አበባ/ፊንፊኔ ወደ ጣልያን ሳይጓዙ እንዳልቀረ ተገለጸ።
የአውሮፕላን አምቡላንሱ ዛሬ በጣልያን ቦለኛ ማረፉ ተረጋግጧል።
??D-CPMU, a Learjet 60 Air Ambulance from ??#AddisAbaba, #Ethiopia heading for Europe as #IFA1018. pic.twitter.com/2Jxo0tJP1k
— Gerjon | חריון (@Gerjon_) January 23, 2021
ትላንትና ማታ የጠቅላይ ሚንስቴሩ ጽህፈት ቤት በዶ/ር አብይ አሕመድ ጤንነት ዙሪያ እየተናፈሰ ያለው ወሬ ሀሳት ነው የሚል መልዕክት በትዊተር ገጹ ማስተላለፉ ይታወሳል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድን ደህንነት አስመልክቶ በማኅበራዊ ሚዲያ የሚናፈሰው ወሬ የሀሰት እንደ ሆነ ሁሉም ሰው እንዲገነዘብ ለማሳሰብ እንወዳለን።#PMOEthiopia
— Office of the Prime Minister – Ethiopia (@PMEthiopia) January 24, 2021
ይሁን እንጂ የአፍሪካ ቀንድ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ዶ/ር በሽር ሀሺ ዩሱፍ፣ ዶ/ር አብይ ከጥቂት ቀናት በፊት ከሱዳን ዲፕሎማቶች ጋር ሲወያዩ ታመው እንደነበረ መረጃው ደርሶኛል ይላሉ።
Abiy Ahmed, who has been sick recently for unknown illness , and not seen in public has responded to #Sudan for the first time & Ethiopian forces & Amhaha militias recaptured already today four villages in the Al-Fashaqa area from #Sudanese forces,
— BASHIR HASHI YUSUF ?? (@BashirHashiysf) January 19, 2021
የሰላም ሚንስቴር ሚንስትር ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በበኩላቸው ዶ/ር አብይ በስራ ገበታቸው እንደሚገኙ በፌስቡክ ገጻቸው ገልጸዋል።
የአፊርካ ቀንድ የፖለቲካ ተንታኝ የሆኑት ራሽድ አብዲ ዶ/ር አብይ ከህዝብ እይታ መራቃቸው ያልተለመደ ሆኖባቸዋል።
Anyone knows where Ethiopian PM Abiy Ahmed is at? He has not been seen in public for days.
— Rashid Abdi (@RAbdiAnalyst) January 24, 2021
አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ዶ/ሩ የፖለቲካ ሴራ እየሸረቡ ሊሆኑ እንደሚችል ይገምታሉ። ሆኖም ሌሎች በርካቶች አገሪቱ በሁሉም አቅጣጫ ከራሷና ከአጎራባቾቿ ጋር ጦርነት በከፈተችበት ወቅት እንዲህ ያለ ዜና ይበልጥ ቀውሱን የሚያባብስ እንጂ የሚበጅ ባለመሆኑ፣ ዶ/ሩ ካሉበት በቀጥታ ስርጭት ለህዝብ መልዕክት በማስተላለፍ አገሪቱን ማረጋጋት ይኖርባቸዋል ይላሉ።
ይህ በእንዲህ እንዳለ በማህበራዊ ሚድያ አንዳንድ ደጋፊዎቻቸው በብልጽግና ውስጥ ክፍፍል መፈጠሩን ይናገራሉ። የዶ/ሩ ደጋፊ አቶ ስዩም ተሾመ የመታመማቸውን ዜና ተከትሎ ትላንትና ማታ በፌስቡክ ገጻቸው ባሰራጩት መልዕክት “በአዲስ አበባ (ፊንፊኔ) እና በኦሮሚያ አመጽ ሊቀሰቀስ እንደሚችል መረጃ ደርሶኛልና ለሚመለከታቸው መልዕክቱን አድርሱልኝ” ብለዋል። (ያ መልዕክት በማግስቱ ከገጻቸው ተነስቷል።) ሌሎች በርካታ የዶክተሩ ደጋፊዎች ዶክተሩ በጤናና በመደበኛ የስራ ገበታቸው እንደሚገኙ በገጾቻቸው አስፍረዋል።

የኢንግሊዝ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ሚ/ር ዶምኒክ ራብ በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከዶ/ር አብይ ጋር መነጋገራቸውን በትዊተር ቢገልጹም በምስል አብረው የታዩት ከም/ጠ/ሚ/ር ደመቀ መኮነን ጋር መሆኑ ብዙዎችን አነጋግሯል።
አቶ ደመቀ መኮነን የቀድሞ የብአዴን፣ የዛሬ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ አመራር ሲሆኑ፣ የውጪ ጉዳይ ሚንስቴር ሚንስትርነት ማዕርግም ደርበው መያዛቸው ይታወቃል።
አቶ ደመቀ ቀደም ሲል በመተከል ይታይ የነበረው ግጭት፣ መፍትሔው ምንድን ነው ተብለው ሲጠየቁ፣ አማራን ከማስታጠቅ ውጪ ሌላ መፍትሔ የለውም በሚለው አወዛጋቢ ምላሻቸው ይታወቃሉ።
ዶ/ር አብይ ለመጨረሻ ግዜ ለህዝብ በአካል የታዩት በመተከል ከአገር ሽማግሌዎች ጋር ሲወያዩ እንደነበር ይታወሳል። በተወያዩ በማግስት በተነሳ ግጭት ከ200 በላይ ሰዎች ተገድለው ማደራቸው በተለያዩ የሚያድያ አውታሮች ተዘግቦ ነበር።
በመተከል በቀጥታ ከሚጋጩት ከአማራና ከጉምዝ ብሔሮች ባሻገር በተዘዋዋሪ የኦሮሞ ታጣቂዎችና የሱዳን ምናልባትም የግብጽ እጅ ሊኖርበት እንደሚችል አንዳንዶች መላምታቸውን ያጋራሉ።
የኢትዮጵያ መንግስት በትግራይ ላይ የከፈተው ጦርነት አገሪቱን ለተለያዩ ጥቃቶች አጋልጧታል፣ ህልውናዋንም አደጋ ላይ ጥሏል ይላሉ አንዳንድ ተንታኞች።
Destination of Air Ambulance reg. ??D-CPMU from ??#AddisAbaba, #Ethiopia was ??#Bologna, #Italy.#IFA1018 pic.twitter.com/foRp26dlQ2
— Gerjon | חריון (@Gerjon_) January 23, 2021
ኦህዴድ-ብልጽግና፣ መሬት አስመላሹ ብአዴንና ህግደፍ-ሻዕቢያ፣ ህወሓትን ለየብቻ መግጠም ስለማይችሉ፣ ተቧድነው ገጠሙት። ሁሉም የጋራ ጠላት እንጂ የሚያስተሳስራቸው የጋራ ሌላ አጀንዳ የላቸውም። ያሸነፉ በመሰላቸው ማግስት፣ እርስ በእርስ መባላት እንደሚጀምሩ ሳይታለም የተፈታ ነበር። ብዙ ዝርዝር ጽፌያለሁ ስለዚህ ጉዳይ፣ ወደዛ አልመልሳችሁም። ፈትቶ የለቀቀው የአማራ ምልሻ / ልዩ ሀይል የአብይ አሕመድ ዋነኛ ራስ ምታቱ ነው። ይህ ሀይል ለ30 ዓመታት ሲፎክርና ሲሸልል ኖረ እንጂ ተኩሶ አያውቅም። አሁን ተደራጅቶ በቆመህ ጠብቀኝ የመተኮስ እድሉን አገኝቷል። ወልቃይትና ራያን እንዲይዝ ተፈቀደሎታል። ይህ የልብ ልብ ይሰጠውና ፊቱን ወደ ሌላ መሬት የማስመለስ ዘመቻ ያዞራል አልነ። እንሆ፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ ልዩ ሀይልና ምልሻውን አሰማርቶ፣ ሲቪሎቹን ለፖለቲካ ትርፍ እየማገደ፣ በሰው ክልል ጦርነት ከፈተ። ኦህዴድና ኦነግም ከጉምዝ ጎን ቆመው እየከተከቱት ይገኛሉ። በጅምላ ተጨፍጭፈው፣ በጭነት መኪና ሬሳቸው እየተነዳ፣ በጅምላ እየተቀበሩ ነው። ሰው ያልዘራውን አያጭድም።
አብይ አሕመድ ያለ የሌለ ጉልበቱን ትግራይ ላይ ጨርሷል። በሌላ ክልል ጸጥታ ሊያስከብር ቀርቶ፣ በትግራይ የጀመረውን መቋጨት አይችልም። ሻዕቢያም ከቁጥጥሩ ውጭ ሆኖ፣ መከላከያ ፈለገ አልፈለገ፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደረ ፈቀደ አልፈቀደ፣ ግድ ሳይሰጠው፣ ያሻውን እያደረገ ነው። ይህ ብልጽግናን ከፈሎታል። መከላከያን ከፈሎታል። በመከላከያና በብልጽግና ቅራኔ ፈጠሯል። አሁን ትግራይ መቀበሪያቸው ብቻ ሳትሆን፣ እርስ በእርስ የሚጫረሱባት የጦርነት አውድም እየሆነች ነው።
የአገር ውስጥ ራስ ምታቱ በቤንሻንጉል ጉምዝና በትግራይ ብቻ አይደለም እየታየ ያለው። በኦሮሚያ ኦነግ ግማሹን ቦታ ተቆጣጥሮታል። የኦህዴድ ተከታዮች ሳይቀሩ፣ ወደ ኦነግ ማዘንበል መርጠዋል። ጃል መሮን የሚከተል ሰራዊት፣ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ሆነዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሚያ ክልል ያሰለጠናቸው ምልሻዎች፣ ጃል መሮን እየተቀላቀሉ ነው። ድፍን ኦሮሞ “እስከዛሬ ለኢዮጵያ የሞትነው ይበቃል፣ ለአገሪቱ እየሞትን በአገሪቱ እየተከዳንና እየተገደልን መኖር የለብንም፣ ከእንግዲህ ትግላችን ለነጻነታችን መሆን አለበት” ብሏል። አብይ አሕመድ ለስልጣኑ ሲል፣ ኦሮሞን ክዶ፣ ከሁሉም ተነጥሎ ብቻዉን ቀርቶ፣ የነፍጠኛ ስርዓት ለመመለስና ለማንገስ እያሸረገደ ነው ብሎ የሚከሰው ድፍን ኦሮሞ ነው። ብንፈልግ እንኳን ኢዮጵያ ከእንግዲህ የመትረፍ እድል የላትም በማለት ኦሮሞ የራሱን ህልውና ወደሚያስከብርበት፣ ጥቅሙን ወደሚያስጠብቅበት ትግል አቅንቷል።
በሌላ በኩል ደግሞ ቅርቃር ውስጥ እንደገባ የተረዳው አብይ አሕመድ፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ምልሻን በማስቀጥቀጥ፣ ነፍጠኛን ለመስበር በማሴር፣ ሱዳን ጦሯን ድንበር ላይ እንድታሰፍር ከሱዳን ጋር መስማማቱን በየሚዳው እየተነገረ ነው። ይህን ሊያደርግ እንደሚችል ከዴይ ዋን ጀምሮ ገምተን ነበር። የልብ ልብ የሰጠው ነፍጠኛ ከሱዳን ጋርም ይተናኮሳል፣ ቢተናኮስም በአብይ ትዕዛዝ ከመከላከያ ድጋፍ አያገኝም የሚል መላምት አስቀምጠን ነበር። እንደተገመተው ብቻ ሳይሆን ከገመትነው ባላይ ነው እየሆነ ያለው። ራሱ አብይ፣ ጦርነቱን የጀመሩትን የአማራ ምልሻና ልዩ ሀይል በይፋ በማህበራዊ ሚድያ ገጾቹ ኮንኗል። የኛን ሰላም የማይሹና የሁለቱ አገራት ወዳጅነት የማይረዱ ናቸው፣ ሲል በሱዳን ወታደር ክፉኛ መቀጥቀጣቸው ሳያንስ ድርጊታቸውን ኮንኗል። ከዛ ብኋላ ነው መከላከያ ለሁለት የተከፈለው። ከአብይ ትዕዛዝ ውጭና ከብርሃኑ ጁላ እውቀት ውጪ፣ በነፍጠኛው የሚመራ የመከላከያ ብራንች ከሱዳን ጋር መጠነኛ ጦርነት ከፍቶ ቆይቷል። አሁንም እንደተፋጠጠ ነው። ምልሻው ብቻዉን ስላልቻለ፣ ጦርነቱን በሁለት ሉአላዊ አገራት መካከል ለማድረግና ከሌላው ህዝብ የድረሱልኝ ጥሪ ለማሰማት ነው ትንኮሳው። በዚህ የብልጽግና መሪዎች አልተስማሙም። ለበርካታ ቀናት አብይ አሕመድ የገባበት አይታወቅም። አንዴ ተመርዟል፣ ሌላ ጊዜ ታሟል፣ ሌላ ጊዜ ታፍኗል የሚል ወሬ እንደሰማን አለን። ምንም ይሁን ምን፣ አገሪቱን አክቲቭሊ እየመራ እንዳልሆነና ለበርካታ ቀናት ከህዝብ እየታ ርቆ እንዳለ ግልጽ ነው።
ይህ ሁሉ ሔዶ ሔዶ የሚጠናቀቀው በአንድ አስቀያሚ እልቂት ነው። በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልል የሰለጠኑ ልዩ ሀይሎች፣ እርስ በእርስ የሚጫረሱበት ግዜ እየመጣ ነው። ፊንፊኔ/አዲስ አበባ እየተሰማ ያለው ተኩስና ፍንዳታ፣ እየታየ ያለው የእሳት ቃጠሎ፣ የፍጻሜው መነሻ ምልክቶች ናቸው። ኢዮጵያ ከሞተችና ከተበተነች ሰነባብታለች። ክፋቱ በሰላም መለያየት ሲቻል፣ በደም አፋሳሽ መንገድ እንዲሆን፣ መንጋው መምረጡ ነው ጉዞዋን ወደ ዩጎዝላቪያ እየቃኘ ያለው።
የህወሓት መሪዎችን በማሰርና በመግደል የተወሳሰበና ለክፍለዘመናት የኖረ ችግራቸውን የሚፈቱ መስሏቸው የነበሩ ሰዎች ዛሬ፣ ትግራይ ላይ ቃታቸውን የሳቡባትን ቀን መርገም ጀምረዋል። ገና ነው፣ ጸጸቱ የምትችሉት አይሆንም።
የተመድ ልኡካን አዲስ በለቀቁት ሪፖርት እንደገለጹት ከሆነ በትግራይ አሁንም አለመረጋጋቱ ቀጥሏል።
ሪፖርቱ እስከተጠናቀረበት ድረስ በመቀለ፣ ሽረና ሸራሮ ዙሪያ በበርካታ ቦታዎች ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው። ልዑካኑ ወደ ሽረና ሽራሮ መጓዝ እንዳልቻለ ገልጿል።
የተባበሩት መንግስታት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (UN OCHA) በታህሳስ ወር በሁለት ቡድን ወደ ትግራይ ተጉዞ ጥናት ካደረገ ብኋላ በለቀቀው ሪፖርት መሰረት፣ በጦርነት በተጎዳው ክልል ውስጥ ከ4.5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች አስቸኳይ የምግብ ዕርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው የገለጸ ሲሆን፣ ከጦርነቱ ወዲህ የምግብ እርዳታ ያገኙ ሰዎች 100 ሺ እንደማይሞሉ ለማወቅ ተችሏል።
በተጨማሪም ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ 2.2 ሚሊዮን የክልሉ ኗሪዎች ከቀያቸው መፈናቀላቸውን ጠቁሟል።
በፀጥታና በቢሮክራሲያዊ መሰናክሎች ምክንያት የከተማ አካባቢዎችን ብቻ ለመገምገም እንደተገደደ የገለጸው የልኡካን ቡድኑ፣ በክልሉ ውሱን የምግብ አቅርቦት እንዳለና ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እየታየ መሆኑን በሪፖርቱ አመላክቷል። የባንክ አገልግሎት ስለመጀመሩ የተገለጸ ነገር የለም።
የልዑካን ቡድኑ በጉብኝቱ “ደካማ የመንግስት አገልግሎቶች፣ አስከፊ የኑሮ ሁኔታ እና የሰብአዊ ጉዳዮች እንዳሉ” መታዘቡን በሪፖርቱ አመላክቷል ፡፡
በርካታ ንብረቶች እንደወደሙና እንደተዘረፉ ያመላከተው ሪፖርቱ፣ በክልሉ ከሚገኙ 40 ሆስፒታሎች ውስጥ በሽተኞችን በአካል ተቀብለው በማስተናገድ አገልግሎት መስጠት የሚችሉት 5 ብቻ መሆናቸውን ገልጿል። ከነዚህ በተጨማሪ አራት ሆስፒታሎች የስልክ አገልግሎት ብቻ ይሰጣሉ ብሏል።
የኤርትራ ወታደሮችም በውጊያው መሳተፋቸውን የኢትዮጵያ መንግስት ሲክድ የቆየ ቢሆንም፣ የንግድ ተቋማትን በመዝረፍ እና ስደተኞችን አፍኖ በመውሰድ የኤርትራ ወታደሮች ተሰማርተው ማየታቸውን ማብራሪያ እንዲሰጡ የተጠየቁ የእርዳታ ሰራተኞች እና ዲፕሎማቶች ገልጸዋል፡፡
የሰሜን እዝ አዛዥ ሜጀር ጄነራል በላይ ስዩም እና በፌደራል መንግስት የተሾመው ጊዜያዊው የመቀለ ከንቲባ አቶ አታክልቲ ወልደስላሴ በተናጠል ከመቀለ ኗሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ እንደሚገኙ ማመናቸው ይታወሳል።
ሰ.ነ.
ምንጭ | ሪፖርተር | ዮሐንስ አንበርብር
የዕዳ መጠኑ ከአገሪቱ አጠቃላይ ምርት (ጂዲፒ) 50.8 በመቶ እንደሆነ ተመላክቷል
የኢትዮጵያ አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች ዕዳ 2.01 ትሪሊየን ብር መድረሱን፣ ሰሞኑን የወጣው የመንግሥት የዕዳ መጠን መግለጫ ይፋ አደረገ።
የገንዘብ ሚኒስቴር ሰሞኑን ይፋ ያደረገው አጠቃላይ የዕዳ መጠን መግለጫ ሰነድ፣ እ.ኤ.አ. እስከ ሴፕቴምበር 2020 ድረስ ኢትዮጵያ ያለባትን አጠቃላይ የአገር ውስጥና የውጭ ብድሮች ዕዳ የሚገልጽ ነው።
በዚህም መሠረት ማዕከላዊ መንግሥት በቀጥታና መንግሥት በሰጠው የብድር ዋስትና የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ከአገር ውስጥና ከውጭ ምንጮች ተበድረው ያልከፈሉት አጠቃላይ ዕዳ 54.7 ቢሊዮን ዶላር እንደ ደረሰ ሰነዱ ያሳያል።
ከአጠቃላይ 54.7 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 28.99 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው ከውጭ የብደር ምንጮች የተገኘ ሲሆን፣ ይህም ሰነዱ በተዘጋጀበት ወቅት በነበረ የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን ተሰልቶ 1.06 ትሪሊየን ብር እንደሆነ ሰነዱ ያመለክታል።
ከተጠቀሰው 54.7 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ፣ ከውጭ አበዳሪዎች የተገኘው ተቀንሶ የሚቀረው 25.7 ቢሊዮን ዶላር ደግሞ ለአገር ውስጥ የብድር ምንጮች የሚከፈል የአገር ውስጥ ዕዳ እንደሆነ ሰነዱ ያስረዳል። ለአገር ውስጥ የብድር ምንጮች መከፈል፣ ያለበት ዕዳ ይህ የዕዳ መጠን ሰነዱ በተዘጋጀበት ወቅት በነበረ የብር የውጭ ምንዛሪ ተመን ተሠልቶ የቀረበ ሲሆን፣ በዚህ ሥሌት መሠረት የአገር ውስጥ የመንግሥት ዕዳ 945 ቢሊዮን ብር እንደሆነ ተጠቅሷል።
አጠቃላይ ከሆነው 54.7 ቢሊዮን ዶላር የአገር ውስጥና የውጭ የዕዳ መጠን ውስጥ 30.6 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነውን በቀጥታ ማዕከላዊ መንግሥትን የሚመለከት ሲሆን፣ ይህም የአጠቃላይ ዕዳው 56 በመቶ ነው።
ከአጠቃላይ የዕዳ መጠን ውስጥ ማዕከላዊ መንግሥትን የሚመለከተው ከተቀነሰ በኋላ የሚቀረው 24.1 ቢሊዮን ዶላር፣ ወይም የአጠቃላይ ዕዳው 44 በመቶ የሚሆነው የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ዕዳ ነው።
ከአጠቃላይ የዕዳ መጠን ውስጥ 25.7 ቢሊዮን ዶላር ወይም 945 ቢሊዮን ብር የሚሆነው ከአገር ውስጥ የፋይናንስ ተቋማት የተወሰደ ሲሆን፣ በአመዛኙም ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተወሰደ መሆኑን ሰነዱ ያመለክታል።
ከተጠቀሰው የአገር ውስጥ ዕዳ 525 ቢሊዮን ብር የሚሆነውን ያበደረው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደሆነ ማስረጃው መረዳት ተችሏል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ከጥቂት ወራት በፊት ይህንኑ ሁኔታ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማስረዳታቸው የሚታወስ ሲሆን፣ በወቅቱ ባደረጉት ንግግርም መንግሥታቸው ተግባራዊ ማድረግ የጀመረው የኢኮኖሚና የፋይናንስ ዘርፍ ሪፎርም ፈጥኖ ባይደርስ ኖሮ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የመውደቅ አደጋ ተጋርጦበት ነበር ማለታቸው አይዘነጋም።
መንግሥት እያደረጋቸው ከሚገኙ ሪፎርሞች መካከል የመንግሥት የልማት ድርጅቶች፣ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተበድረው ያልከፈሉትን ዕዳ ቀስ በቀስ ወደ መንግሥት ማዘዋወር አንዱ ተግባራዊ መደረግ የጀመረ የመፍትሔ አማራጭ መሆኑን ሪፖርተር ያገኛቸው ሌሎች መረጃዎች ያመለክታሉ።
ከአጠቃላይ የአገሪቱ ዕዳ ውስጥ ለውጭ አበዳሪዎች የሚከፈለው 28.99 ቢሊዮን ዶላር ወይም 1.06 ትሪሊዮን ብር ግን አለመክፈል የሚቻልበት ሁኔታ ዝግ በመሆኑ፣ የኢትየጵያ ደግሞ በማክሮ ኢኮኖሚ መዛባት ውስጥ በመውደቁ፣ ለመንግሥት ከፍተኛ የራስ ምታት ሆኗል፡፡ መንግሥትም ይኼንኑ ሕመሙን ሳይሸሽግ በተደጋጋሚ ጊዜ ሲገልጸው መቆየቱ ይታወሳል።
ይኼንን የውጭ ዕዳ የመክፈያ ጊዜ እንዲራዘም ከመደራደር ውጪ የመክፈሉ ግዴታ የማይለወጥ እንደሆነ ባለሙያዎች ይገልጻሉ። ይህንን የውጭ ዕዳ ኢትዮጵያ መክፈል እንደማትችል ከተረጋገጠ ደግሞ አገሪቱን ጥቁር መዝገብ ውስጥ እንድትሰፍርና በቀጣይ የውጭ ብድር ፍላጎቷ በር የሚዘጋ ሁኔታን ሊፈጥር እንደሚችል ባለሙያዎች ያስረዳሉ።
የውጭ ዕዳን ሙሉ በሙሉ ማሰረዝ አስቸጋሪ መሆኑን የሚገልጹት ባለሙያዎቹ፣ የቀደሙ የኢትዮጵያ መንግሥታት በአሁኑ ወቅት ከፈረሰችው ሶቪዬት ኅብረት ተበድረው ያልመለሱት ዕዳ፣ አሁንም ድረስ በዓለም የገንዘብ ድርጅት (አይኤምኤፍ) የኢትዮጵያ የውጭ ዕዳ ተብሎ እስካሁን ተመዝግቦ እንደሚገኝ ይገልጻሉ።
አገሪቱ ካለባት የውጭ ዕዳ ውስጥ ብቻ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ድርሻ 36 በመቶ መሆኑን ሰነዱ የሚያመለክት ሲሆን፣ 54.7 ቢሊዮን ዶላር ከሆነው አጠቃላይ የአገሪቱ የአገር ውስጥና የውጭ ዕዳ ውስጥ 44 በመቶው ወይም 24.1 ቢሊዮን ዶላር የሚሆነው የመንግሥት ልማት ድርጅቶች ዕዳ እንደሆነ ይጠቁማል።
አጠቃላይ የመንግሥት ዕዳ የኢኮኖሚ ዕድገት መለኪያ ከሆነው አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት (GDP) 50.8 በመቶ እንደሚሆን መረጃው ያመለክታል። ከዚህ ውስጥ የመንግሥት ልማት ድርጅቶች የአገር ውስጥ ዕዳ ለብቻው ከአጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት አንፃር 12.5 በመቶ ድርሻ ይዟል።
የአገሪቱ የውጭ ዕዳ አማካይ የመክፈያ ጊዜ 15 ዓመት መሆኑንም መረጃው ያመለክታል።
ከዚህ ጦርነት ብኋላ፣ መደምደሚያው ምንም ይሁን፣ ኢትዮጵያ እንደ አገር የመቀጠል እድሏ ዜሮ ሆኗል። አክትሞላታል። ህወሓት ጦርነቱን ቢያሽንፍ እንኳን ተመልሶ አገር በማስተዳደር ረገድ ከእንግዲህ ድርሻ ይኖረዋል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው። ህዝቡም ህወሓትም ያንን እድል/ሁኔታ ዳግም የሚፈልጉት አይመስለኝም። ባንዳዎቹና ግልገሎቹ ከቀናቸውም ኢትዮጵያን ማስቀጠል አይችሉም። ዝርዝሩን አቀርባለሁ።
የኦሮሚያ ብልጽግና፣ የአማራ ብልጽግናና የሻዕቢያ አላቻ ጋብቻ በልጅነቴ እየሰማሁት ያደግሁት የዘንዶ ታሪክ ያስታውሰኛል። እነዚህ ሶስቱ ሀይሎች በተናጠል ከህወሓት አንጻር ሲታዩ ቁጫጭ ናቸው። በጋራ ካልሆነ በተናጠል ህወሓትን መሞከር ቀርቶ ማሰብ የማይታሰብ ነው። ጋብቻቸው ስትራቴጂካል ነው፤ በቅድሚያ በጋራ ተረባርበው ይጥሉታል፣ አንደኛው ለስልጣኑ፣ ሁለተኛው ለመሬቱ ሶስተኛው ለበቀል። ሶስቱም ግን ሌላ የሚያመሳስላቸው አንድ ወሳኝ ባህሪ አለ። ሶስቱም ኤክስፓንሺንስት/ተስፋፊ ና ኦፖርቹኒስቲክ ናቸው። በለስ ቀንቷቸው ህወሓትን ካስወገዱ ወይም ያስወገዱ ከመሰላቸው፣ በማግስቱ ሌላ የመስፋፋትና እርስ በእርስ የመዋዋጥ ጌም ይጀምራሉ፥
1 የኦሮሚያው ብልጽግና ሁለቱን የሚፈልጋቸው ለሚቀጥሉት አስርት አመታት ስልጣን ላይ ለመቆየት መጠቀሚያ ለማድረግ ነው። ካልጠቀለላቸው ይህን ማሳካት አልችልም ብሎ ነው የሚያስበው። ከእርሱ ፈቃድ ውጪ መግባትና መውጣት የማይችሉ፣ ወዶና ፈቅዶ ብቻ ስልጣን የሚሸነሽናቸው አሻንጉሊቶች መሆን የግድ አለባቸው። አለበለዚያ የቀድሞ ጓዶቻቸውን ጉድጓድ ይጋራሉ። በሀሳብ ደረጃ፣ ሶማሊያን፣ ጅቡቲ፣ ኤርትራን፣ ሱዳንን ጠቅልለን በምስራቅ አፍሪካ ታላቅ “አገር” በገዳ አምሳል እንመሰርታለን የሚል ጽንፍ የረገጠ ተስፋፊ አጀንዳ ይዞ የተነሳ ቡድን መሆኑ አይዘነጋም።
2 የአማራ ብልጽግና የመሬት ይገባኛል ጥያቄ በወልቃይትና በራያ አይመለስም። በሰሜን በኩል አሰብን ይጠይቃል። ዳር ድንበሬ ቀይ ባህር ድረስ ነው ይላል። ከኦሮሚያም ሰፋፊ የሚጠይቃቸው ግዛቶችና ከተሞች አሉት። በድሮዋ የኢትዮጵያ ካርታ የሚታየው የአገሪቱ ክፍል በጠቅላላ የአማራ ግዛት ነው፤ የአማራ መሬት ነው ብሎ ያምናል። ጠንካራ ኢኮኖሚና ጠንካራ ሰራዊት በመገንባት ማእከሉን ዳግም መቆጣጠር ይፈልጋል። ወይም መቆጣጠር አለብኝ ብሎ ያስባል። ካለበለዚያ ህልውናው ሁሌም አደጋ ላይ እንደወደቀ ይሰማዋል። እየተሽሎከልለከና በሁለት ሶስት ፓርቲዎች እየተደራጀ ጡንቻውን ማፈርጠም ከህዝብ ያልተሰወረ ስልቱ ነው።
3 ኢሳያስ ህወሓት በተወገደ ማግስት ከኋላ ሆኜ እዘውራለሁ፣ ኢትዮጵያን በእጃዙር እገዛለሁ ብሎ ነው የሚያምነው። እየኮረኮመ የሚያሰራውን ከመጋረጃው ጀርባ በቡችላው አብይ አማካኝነት መሾም መቻል ይሆናል ነው ምኞቱ። ካልሆነ ከወዲ ዜናዊ ጋር የተጀመረው ጸብ በሲዝን ሁለት ይቀጥላል።
አስተዋላችሁ? በመካከላቸው እርስ በእርሳቸውም ሆነ፣ ከነሱ ውጪ ካለው ቡድን ጋር በእኩልነት መኖር የሚያስችል አጀንዳና የስነልቦና ቅድመዝግጁነት የላቸውም። ባህሪያቸው አንዱ ሌላኛውን ውጦ መዘንደድ ነው። ህወሓት በክልል ቆራርጦ ኢትዮጵያን ቢያሳንሳትም፣ በህግ አውቶኖሚውን ለክልሎች ሰጥቷል። ተጠቅመውበታል አልተጠቀሙበትም ሌላ ጉዳይ ሆኖ፣ ካልተመቻቸው እስከመገንጠል ድረስ ልዩ መብት የሚያጎናጽፍ ህገመንግስት ሰጥቷቸዋል። ትናንሽ ግን አውቶኖመስ የሆኑ የፖለቲካ ዩኒቶች (ክልሎችና ልዩ ዞኖች) በእኩልነትና በመፈቃቀድ የተመሰረተ አብሮነት ሲኖራቸው ብቻ አገር በጋራ ያስቀጥላሉ፤ ተብሎ ለ30 አመታት (ግማሹ የኢትዮጵያ ህዝብ የተመረተበት አመታት) ተሰርቶበታል። ኖረውበታልም።
ገሚሱ የኢትዮጵያ ህዝብ ከዚህ የአስተዳደር ሲስተም ውጪ ሌላ የሚያውቀው ነገር የለም። እንደ አይንአር በአንዴ ጠርገህ ልታጸዳውና ሊረሳ የሚችል ጉዳይ አይደለም። እናም በማዕከላዊ መንግስት ይሁንታና ፈቃድ የሚሾሙ የሙስጠፌ፣ የተመስገን ምናምን አይነት ታማኝነታቸው ለአንድ ግለሰብ የሆኑ መሪዎችና ለይስሙላ ብቻ የሚሰየሙ ምክር ቤት ይኖራችኋል፣ ቢባሉ ማናቸውም አሜን ብለው አይቀበሉትም። የቀመሷት ነገር አለች የምትጥም፣ የምትጣፍጥ። ማንነቴን፣ ባህሌን፣ ቋንቋዬን፣ እምነቴን፣ የሚሏት ነገር።
አንዱ ሌላኛውን ሰልቅጦ ለመዘንደድ ሲቧጨቁ፣ ሌላው ለማንነቱ ሲንተጋተግ፣ ሰላም፣ መረጋጋት፣ ልማት፣ አገር፣ ብሎ ነገር ፈጽሞ ያከትምለታል።
ድሕረ ህወሓት የምትኖረው ኢትዮጵያ የፈራረሰች ኢትዮጵያ ብቻ ናት። የታሪክ መጻህፍት ላይ ብቻ የምታገኟት። ፍጻሜዋ ያላማረ። በ21ኛው ክፍለዘመን በእርስ በእርስ ጦርነት እስከዘላለሙ ያሸለበች ኢትዮጵያ።
ይህ እንዳይመጣ ነበር፣ በድርድርና በውይይት አብሮ የሚያኗኑር መላ ፈልጉ፤ ካቃታችሁ ያለው የፌደራሊዝም ስርዓት ይቀጥል ወይስ በሌሎች አማራጮች (ጂኦግራፊ መሰረት ያደረገ ፌደራሊዝም፣ ፍጹም አሃዳዊ ወዘተ) እንተካው ብላችሁ ህዝቡን ጠይቃችሁ በሪፈረንደም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት ያግኝ፤ ብለን ስንመክራችሁ የኖርነው። በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተና የብዙሃን ይሁንታ ያገኘ ስርዓት ከመመምስረት ውጪ ሌላ አምራጭ የላችሁም ስንላችሁ የኖርነው በምክንያት ነው። ኢትኒክ ፌደራሊዝም በጉልበት ተጭኖ ሙሉ ተቀባይነትን እንዳላገኘ ሁሉ፣ አሃዳዊ ስርዓት በጉልበት ተጭኖ ሙሉ ተቀባይነትን አያገኝም። ግማሹን የህበረተሰብ ክፍል ያገለለ ስርዓት ደግሞ መቼም ቢሆን አይጸናም። እናም ከወዲሁ እላለሁ …
ነፍስ ይማር!
ጦርነቱ ትክክል ነው፣ ከህወሓት ጋር ነው። ወንጀለኞችን ለህግ ለማቅረብ የሚደረግ ህግ የማስከበር ስራ ነው። ብላችሁ ለምታምኑ ህሊናችሁን እንድትፈትኑት የሚጋብዝ ጽሁፍ ነው። 95 ሚልዮን ለ5 ሚልዮን፣ ይጥፉ ወይስ እንጥፋ፣ ወዘተ በሚል የታወረ እይታ የምታራምዱ ከሆነ፣ ይህን ማንበብ አይመከረም እዚሁ አቁሙ። አላማው ምን ያህሉ በተሳሳተ መረጃ፣ የተሳሳተ አቋም እንደያዘ ለማወቅ ነው። ሁላችንም አቋማችንን እያጠራን እንድንሔድ ይረዳናል።
ይህ ሁሉ የተደረገውና እየተደረገ ያለው ጥቂት በህግ የሚፈለጉ ሰዎችን ለመያዝ ወይስ ትግራዋይን ለመስበር? የፈለገውን ያህል ኪሳራ ያስከትል (ትግራዋይ ተሰብሮም ይሁን) ደንታ የለንም ከሆነ መልሳችሁ አንድ ነገር ነው። ጥቂቶችን ለህግ ለማቅረብ ይህን ያህል ርቀት መጓዝ ትክክልና ተገቢ ነው ብላችሁ ከሆነ የምታምኑትና እርምጃውን የምትደግፉት ዝምታችሁ መልስ ይሆናል። እንደነ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው “የለም ይህ ትክክል አይደለም፣ እብደት ነው” የምትሉ ከሆነ ደግሞ አቋማችሁን አጥርታችሁ ይህን ጦርነት ለማስቆም ጫና መፍጠር ይጠበቅባችኋል።
በበኩሌ አብይ ህግ አስከባሪ ሆኖ በህግ ሊፈልጋቸው የሚችሉ ወንጀለኞች ይኖራሉ ብዬ አላምንም። ምናልባት የኢትዮጵያ ህዝብ እርሱንና ጋሻ ጃግሬዎቹን ወደ ህግ ማቅረብ የሚፈልገውን ያህል ከህወሓት ባለስልጣና ሌሎችም በህግ ሊጠይቃቸው የሚፈልጋቸው ሊኖሩ ይችላሉ። አሉም። ነገር ግን አብይ ከነሱ ተሽሎ ህግ አስከባሪ ነኝ የሚልበት ምንም የሞራል መሰረት የለውም ብዬ አምናለሁ። በደም የተጨማለቀ በብዙ ወንጀል የሚፈለግ፣ በገለልተኛ አካል ብዙ መጣራት ያለባቸው የህዝብ ጥያቄዎች አሉ። የአማራ መሪዎች ሞት፣ የኢንጅነር ስመኘው ግድያ፣ የነጄነራል ሰዓረ ሞት፣ የአርቲስት ሀጫሉ ግድያ፣ የዜጎች በየቦታው መፈናቀል በየተለይ አዲስ አበባ ዙሪያና ኦሮሚያ፣ የንጹሀን ዜጎች በየቦታው መሞትና ሌሎችም ሁሉም በገለልተኛ አጣሪ ኮሚሽን ተጣርተው ወንጀል ፈጻሚዎች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው። አገሪቱ አሁን የገባችበትን ጦርነት ጀስቲፋይ የሚያደርግ በቂ ምክንያት ስለሌለ፣ ወደ ጦርነት የከተቱን ተጠያቂ ሰዎች ተጣርቶ ለፍርድ ሊቀርቡ ይገባል። እስከዛው ያለ በቂ ምክንያት የተገባው ጦርነት አንድን ሉአላዊ ህዝብ ለማንበርከክ የተቃጣ ወረራና ጥቃት ነው ብዬ ነው የማምነው። ለዚህም ነው ከትግራዋይ ወገኔ ጎን የቆምኩት። ተሳሳትኩ?
