ጽምዶ

ጽምዶ የሚባለው የፖለቲካ አሰላለፍ አዲስ አይደለም። የትግራይ ጦርነት ሲጀመር ጽምዶ1 ነበር። አጻማጁ አጀንዳ “በቀል” ነበር። ያኔ ከአማራ ምልሻ (ኋላ ላይ ቁመናውን ገንብቶ ፋኖ ሆነ) እና ከሻዕቢያ ጋር የተጻመደው ብልጽግና ነበር። ያልተጻመደው ህወሓት ነበር። ለሶስት ገጠሙት። ከህወሓት አልፈው የትግራይን ህዝብ ጨፈጨፉት። የህዝቡ መገፋት ለህወሓት ትልቅ ጉልበት ሆነውና ከህጻን እስከ አዛውንቱ ዘመተ። ተከታከተ ወዘተ። በቀዳማይ ጽምዶ ታሪክ ይቅር የማይለው ግፍ ተፈጸመ።

አሁን ጽምዶ 2 ላይ ነን። ህወሓት፣ ሻዕቢያና ፋኖ ተጻምደው ብልጽግናን አሸወይና ሊያሰኙት ነው። አጻማጁ አጀንዳ ሌላ ነው። ከበቀል ቦርቀቅ ያለ ነው። ስርዓቱን ቀጥቅጦ ተበቅሎ፤ ስልጣን፣ ፖለቲካን እና ኢኮኖሚውን መቆጣጠር ነው። ግን ግን እንደ ጽምዶ1 የብዙ ሰዎች ድጋፍና ይሁንታ ያገኘ አይደለም። ያም የተለያየ ምክንያት አለው።

1. ብልጽግና ራሱን ሌጅቲሜት መንግስት አድርጎ ስለሚቆጥር፣ ጽምዶ2ን እንደ ህገወጥነት፣ አገር ክህደት፣ ባንዳነት፣ ወዘተ ስም ሰጥቶ ራስን የማዳን የጣረሞት ፕሮፓጋንዳ ይሰራበታል።

2. ከብልጽግና ጋር የተጣበቁ አጋሮች፣ ሀሰተኛ የፖለቲካ ፓርቲዎች ወዘተ እየመጣ ያለውን ነገር ስለሚያውቁ፣ የብልጽግና መንግስት ከተገለበጠ እነሱም ዋስትናቸው ዜሮ እንደሆነ ስለሚያውቁ፣ የብልጽናውን ፕሮፓጋንዳ እንደወረደ ከማስተጋባት ጀምሮ የራሳቸውን የተቃውሞ ዘመቻ በየፊናቸው፣ በየቋንቋቸው ያስተጋባሉ። ኢዜማም በለው አብን ወይም ቀንበጧ ስምረት የተቃውሟቸው ምክንያት ይህ ነው። በተለይ ስምረት የገባችበት ጉድጓድ እንደተማሰ ነው የምትቆጥረው።

3. የኤርትራ አክቲቪስቶችና ተቃዋሚዎች ጽምዶ2ን ከጽምዶ1 በበለጠ ሁኔታ ይቃወሙታል፣ ያወግዙታል። ጽምዶ ባጠቃላይ (አንድም ሁለትም) የኢሳያስ አፈወቅርቂ ዕድሜ ማራዘሚያ እንክብል ነው። ያኔም ለስርዓቱ ካላቸው ተቃውሞና ነገ ስልጣን ተረክበው ኤርትራን ለመምራት ካላቸው ተስፋ የመነጨ ተቃውሞ ነበራቸው እንጂ በኤርትራ የሉኣላዊነት ጉዳይ ላይ በባህር በሮቿ በቀይባህር ዘበኝነቷ ወዘተ ከሻዕቢያ የተለዩ ሁነው አይደለም። ጽምዶ2 ግቡ ከተሳካ የሻዕቢያና የኢሳያስ የስልጣን ዘመን ይራዘማል፣ የተቃዋሚ ሃይል ይዳከማል፣ ድምጹም ይሰልላል። አሁን እነዚህ አክቲቪስቶችና የኢሳያስ ተቃዋሚዎች ስለ ጽምዶ2 ተቃውሟቸውን ሲያሰሙ፣ ጣታቸውን የሚቀስሩት ህወሓቶች ላይ ነው። እንዴት አንደር ዘ ቡሽ ትጫወቱብናላችሁ ዓይነት።

4. ቤዛቸውን ትግራይ ላይ ያደረጉ ትግራይ ውስጥ ሆነው የሚታገሉ የትግራይ ተቃዋሚዎች ጽምዶ2ን የሚቃወሙት ባብዛኛው ከኤርትራውያን አቻዎቻቸው የተለየ አይደለም፤ ከአንድ ምክንያት በስተቀር። ይኸውም የትግራይን ህዝብ እንደዛ የገፋው ሻዕቢያ ዛሬ እንደ ትግል አጋር ወይም እንደ መድህን ልንቀበለው ፈጽሞ እንዴት ይቻላል? የሚል ነው። ህወሓት እነሱን እንደ አስጊ ሃይል ቆጥሮና አግልሎ ከሻዕቢያና ፋኖ ጋር አብሮ ለመስራት መፍቀዱ አስቆጥቷቸዋል። ጥያቄያቸው ደግሞ በአብዛኛው ሲቪል ትግራዋይ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ስለሆነ የትግራይን ጉልበት ለሁለት ገምሶታል። ጦርነት ከተነሳ ይህ ለብልጽግና ቢግ ፕላስ ነው።

5. የመጨረሻው የጽምዶ2 ተቃዋሚ የባሩድ ሽታና የተኩስ እርምታ የሰለቸው የትግራይ ህዝብ ነው። ጦርነት የሰለቸው ማለት አልችልም፣ ምክንያቱም ጦርነቱ እስከዛሬ ድረስ እንደቀጠለና አቁሞ የማያውቅ ነውና። በጽምዶ2 ተመልሶ ሊመጣ ይችላል ብለው የሚሰጉት የባሩድ ሽታ፣ የተኩስ እሩምታ፣ እና የድሮን አውዳሚ ቦምቦችን ነው። የሲቪልያን ይህን መቃወምና ሰላምን መሻት የሚጠበቅ ነውና ተቃውሞው ተገቢ ሊሆን ይችላል። ነገር ግን ያልተደራጀህ፣ መሻትህን የምታስፈጽምበት ተቋም እና አደረጃጀት ከሌለህ፣ ምኞትህ ምኞት ብቻ ሆኖ ይቀራል። ወይም ጸረ ህልውናህ ሊሰራ ይችላል። ምክንያቱም ጦርነቱ ከተነሳ እንደከዚህ ቀደሙ በሙሉ ልብነት አሸንፎ ለመውጣት የመታገል ስሜት አይኖርም። ይህን ለብጽግና ሌላኛውና ዋነኛ ቢግ ፕላስ ይሆናል ማለት ነው።

እንደኔ እምነት የጽምዶ ፖለቲካን ለመረዳት ዩ ሀቭ ቱ ፎሎው ዘ መኒ። በጣም ቀላል ነው። በፖለቲካ ቋሚ ወዳጅ ወይም ቋሚ ጠላት የለም የሚባልበት ምክንያት ይችው ናት። መኒዋ የለችበትን ለመረዳት ደግሞ በነሱ ጫማ ላይ ቆመህ፣ የኔን ጥቅም የምታስከብረው የትኛዋ አቋም፣ ስልት፣ ወይም የትግል ስትራቴጂ ናት ብለህ መጠየቅ ብቻ ነው። ከ1 እስከ 5 የተዘረዘሩት ጽምዶ2ን የሚቃወሙና እዚህ ያልተዘረዘሩት ጽምዶ2ን የሚደግፉ፣ ለምን እንደሚቃወሙና እንደሚደግፉ ለማውቅ፣ ያቺን ጥያቄ በነሱ ቦታ ሆኖ ማንሳት ብቻ ነው።

የጽምዶ ፖለቲካን የምረዳው በዚህ መልኩ ነው ለማለት ነው።

ሃቅ ሃቁን ብቻ እናውራ ከተባለ …

ሃቅ ሃቁን ብቻ እናውራ ከተባለማ …
የፖለቲካ ወይም የኢኮኖሚ ፍልስፍና እይታቸውን ፈጽሞ የማልስማማበት፣ ነገር ግን በጣም የማደንቃቸው ባለ ከባድ ሚዛን አስተማሪዎቼ (ተጽእኖ ፈጣሪዎች) በምድር ላይ ሁለት ሰዎች አሉ/ነበሩ። መለስ ዜናዊ እና አያን ራንድ። የአትላስ ሽራግድ እና ዘ ፋውንቴን ሄድ ደራሲዋና ፈላስፋዋ ራንድ፣ በጆን ጋልት እና በሃዋርድ ሮርክ አማካኝነት የምታስተላልፋቸው፣ ፍጹም የማታወላዳበት የኦብጀክቲቪዝም ፍልስፍና ብላ የምትጠራው ግለሰባዊነትን እስከጥግ ድረስ ለጥጣ የምታወድስባቸው ስራዎቿ በብዙ የማልስማማባቸው (አንዳንዴ የምጸየፋቸው ጭምር) ቢሆንም፣ ብዙ የተማርኩባት እና የማደንቃት ጸሃፊ ናት። ስለ ራንድ በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን። አሁን ስለ መለስ እናውራ።
ራሳችንን ካልዋሸን በስተቀር፣ መለስ በተለይ በኢኮኖሚክስ ትንተናው አንድን ትውልድ አነሳስቷል፣ ቀርጿል፣ ቢባል ማጋነን አይሆንም። በመለስ ዘመን ስለ ዴቨሎፕመንታል ኢኮኖሚክስ የማይደሰኩር ፖለቲከኛ፣ ምሁር፣ ተማሪ፣ ካድሬ ወዘተ አልነበረም ቢባል ማጋነን አይሆንም። ስለ ኢኮኖሚክ ፓራዳይም፣ ስለ ግሪን ኢኮኖሚ፣ ስለ ኒዮሊበራሊዝም፣ ስለ ኪራይ ሰብሳቢነት (ሬንት ሲከርስ) ወዘተ የማይወራበት፣ የማይተነተንበት እና የማይተችበት ቀን አልነበረም። በፖለቲካው ልንቃወመውና ልንጠላው እንችላለን (በዛም ረገድ ሻምፕዮን እንደነበር አሁን እየበራልን ቢሆንም)፣ በኢኮኖሚክስ እውቀቱ፣ የትንታኔ ብቃቱ፣ ከኢንግሊዝኛ ወደ አማርኛና ትግርኛ የመመለስ ብቃቱ ግን ማንም ሰው አይክደውም።
እስኪ እውነት እንናገር እና፣ ስለ ርዕዮተ አለም፣ ስለ ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ፣ ስለ ኢኮኖሚክ ፍልስፍና ከመለስ ዘመን ወዲህ በማህበራዊም በሉት በመንግስት ሚድያ ተወርቶ ያውቃል? ያ አጀንዳ፣ ያ ሙግት፣ ያ ትችት አልናፈቃችሁም? በነ ኮንፍዩዝድ እና ኮንቪንስ ዘመን፣ መደመር ከምትለው የ3ኛ ክፍል አርቲሜቲካ የዘለለ አንዲት ቃል ሳንሰማ አስር አመት ሊሞላን ደረሰ። በመለስ ዘመን ፎር ግራንትድ ወስደነው የነበረ ጸጥታ፣ የማዕከላዊ መንግስት ጥንካሬ፣ ወዘተ ከመለስ ወዲህ አፈርድሜ ግጦ፣ ወሬያችን እና ኑሯችን ሁሉ ስለ ጦርነት ብቻ አልሆነም? እንደ ዘመነ ደርግ፣ ብልጽግና እድሜዋን በጦርነት ፈጀችው። ቅቤው ኢንስፓየር ያደረገው ትውልድ ቢኖር እነ ምናምን ድሪምስ እንደሚባሉት አነቃቂ እና ሰባኪ ነን ባዮችን ብቻ ነው። (የበርትራንድ ራስል ፍልስፍና መጽሃፍ ካነበባችሁ፣ እንዲህ አይነት ሰዎች የሚበራከተቱ ከአንድ ማህበረሰብ ውድቀት እና ስብራት ብኋላ መሆኑን ትገነዘባላችሁ። ትኩረት ሁሉ ራስን ለማጽናናት፣ ቀኑን እንደምንም ለማሳለፍ ይሆናል። የስቶይሲዝም ፍልስፍናን በዚህ መልኩ ነው ሩስል የሚገልጸው። ግሪኮች በጦርነት ተሸንፈው አገራቸው እንክትክት ስትል እና በሌሎች ቁጥጥር ስር ስትወድቅ፣ ያ ሰማይ ምድሩን የቧጠጠው፣ ከአተም እስከ አጽናፈ አለም የቃኘው ፍልስፍናቸው ከስሞ በነ ኢፒኲሬስና ኢፒክቲቱስ የሃፒነስ ፍልስፍና ተተካ። አይንህን ጨፍነህ የልብ ትርታህን ካዳመጥክ፣ ጭንቀትህ ሁሉ ውልቅ ብሎ ሲሔድ ታያለህ። የደስታ ምንጭ ወደ ውስጥ መመልከት ነው። ወዘተ)
መለስ በአደባባይ ጭምር ደረቱን ነፍቶ እየተከራከረ የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ ከኒዮሊበራላይዝም ታደገው። በየጊዜው የሚቀርብበትን ጫና ተቋቁሞ፣ ተከራክሮ፣ እነ ጆ ስቲግልቲዝ አስደምሞ፣ የኢኮኖሚ ሉኣላዊነቱን አስከብሮ አለፈ። (አገሪቱ በየጊዜው የምትቀበለውን ምጽዋት ወደጎን ብለን)። ዛሬ አንድም ሳይቀር ገበያው በሙሉ ተበርግዶ ላለው ሲሰጥ፣ አንዲትም ክርክር አልተደረገም፣ ወይ አመክንዮ አልቀረብም። እንደሾካካ የተባለቱን ፈጽመው ጭጭ አሉ። ሃሳብ የደረቀበት ስርዓት እና ዘመን ላይ ሆነህ እንደ ወ/ሮ ጊዜሽወርቅ ተሰማ በድፍረት ምስክርነትህን ስትሰጥ … ያምርብሃልና የኔን እንሆ አልኳችሁ።

ኢትዮጵያ የ ዘረመል ለውጥ የተደረገባቸውን 3 የበቀሎ ዝሪያዎች በስፋት አምርታ ለገበያ ለማቅረብ ተስማማች