Solomon Negash
  • Selam!
  • Books
  • Codes
  • About
  • Click to open the search input field Click to open the search input field Search
  • Menu Menu

ከእርስ በእርስ ጦርነትና የዕልቂት አዙሪት ለመውጣት

Read the English version here. በኢንግሊዝኛ ለማንበብ ይህን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ።

1. አልፋና ኦሜጋ የሆነውን በአገር ሉኣላዊነት ብጽኑ የማመን መርህ ይኑረን። የሁሉም መነሻ የአገርንና የህዝብን ሉኣላዊነትን ማክበርና መጠበቅ ነው። በውጭ ሃይል እየተጠመዘዝክና እየታገዝክ፣ የአገርህን ሉኣላዊነት ሸጠህ፣ ከማንም ከምንም በምንም ነጻ ልትወጣ አይቻልህም። በተለይ ደግሞ ለሶስት አስርት አመታት አገሪቱን ለማፈራረስ በግልጽ ተግቶ ሲሰራ ከኖረው ሻዕቢያ ጋር መሞዳሞድ፣ ውሎ አድሮ የሚቋጨው በሌላ ግጭት መሆኑን ከትላንትም ከዛሬም ታሪክ መማር ያስፈልጋል።

2. ሉኣላዊነት የማክበርና የመጠበቅ መገለጫው፣ በስራ ላይ ያለውን ህገመንግስት ማክበርና ማስከበር ነው። ህገመንግስቱ መቀየር ወይም መሻሻል ካለበትም፣ ህጋዊ አሰራሩን ተከትሎ እስኪሻሻል ወይም እስኪቀየር ድረስ፣ በዛ ህግ መገዛትና ለዛ ህግ መቆም ግድ ይላል። የአንድ አገርና የፖለቲካል ማህበረሰብ ምሰሶ ህገመንግስቱ ነውና።

3. ይኽም ማለት ህገመንግስታዊ ጥያቄዎች ሁሉ፣ ህገመንግስታዊ ምላሽ እስኪያገኙ ድረስ፣ እያንዳንዱ ግለሰብና ቡድን ኢህገመንግስታዊ የሆኑ የአጭር ግዜ የመፍትሔ እርምጃዎችን ከመውሰድ ሊቆጠብ ይገባል ማለትነው ። ዜጎች በማንነታቸው ምክንያት ከቀያቸው መፈናቀል መቆም አለበት። በጉልበት የተያዙ ቦታዎች ወደ ህገመንግስታዊ ስፍራቸው መመለስ አለባቸው። ወዘተ።

4. ሁሉም በየፊናው አሁን እየሔደበት ያለው መንገድ፣ ከመተላለቅና በመተላለቅ አዙሪት ከመጠመድ ውጪ የትም እንደማያደርሰው መገንዘብ አለበት። ይህን ለመገንዘብ ደግሞ ከባድ አይደለም። መፍትሔውም ሁሉም ኢጎዉን፣ ግብዝነቱን፣ ጥራዝነጠቅነቱን፣ ምናምኑን ትቶ፤ ትላንት አሻፈረኝ ወዳለውና ወዳጣጣለው ሁሉን አቀፍ አገራዊ የውይይትና የድርድር መድረክ መመለስ ነው። አገሪቱ እንደአገር ቀጠለችም አልቀጠለች፣ ነገ በሰላም ለመኖር፣ ከውይይትና መነጋገር ውጪ ሌላ ምንም (ይደገም፣ ሌላ ምንም) አማራጭ የለም። ደም ተፋስሰህ፣ ንጹሃንን አስጨርሰህ፣ ጉልበትህ ከዛለ ብኋላ በጉልቤዎች እየተጠመዘዝክ ለድርድር መቀመጥህ ላይቀር፤ ዛሬ ሰልጠን ቆፍጠን በልና በራስህ ተነሳሽነት ሞክረው። ታተርፍበታለህ። በታሪክ ስህተት ያልሰራ መንግስት፣ ህዝብን ያላፋጀ ቡድን፣ ያልተጋጨ ህዝብ የለም። ነገር ግን ብዙዎች በመነጋገር ብቻ የትላንት ጠባሳቸውን ሽረው፣ በጋራ ወደፊት መራመድ ችለዋል።

5. እርግጥ ነው፣ አብይ አሕመድ ዛሬም ለድርድር፣ ወይይትና መነጋገር አለርጂክ ነው። ተገዶ በጆሮው እየተጎተተ ካልሆነ በስተቀር፣ ውይይትን እንደተሻለ አማራጭ የሚያስበው ነገር አይሆንም። እንዲህ ያለውን ሃሳብ ቢፈልገው ኖሮ፣ ያኔ ያላንዳች ስራ በዜጎች ልብ በነገሰበት በዛ የስካር ዘመን፣ ይህን ማድረግ ይችል ነበር። የተጣሉትን አስታርቆ፣ የማይነጋገሩትን አነጋግሮ፣ ሁሉንም አደራድሮ፣ የጋራ መፍትሔ በጋራ አፍልቀው፣ አገሪቱ ወደኋላ የምትሸመጥጥበትን ሳይሆን ወደፊት የምትድህበትን መንገድ መፍጠር ይቻል ነበር። ከትውልድ ወደ ትውልድ የሚተላለፍ ጠንካራ ሌጋሲ ትቶ የማለፍ እድሉ ያኔ አመለጠ። ፍላጎቱ ንጉስ መሆን ነበርና የሆነው ሁሉ በተቃራኒ ነበር። ዛሬም ከዚህ የተለየ ያደርጋል ተብሎ አይጠበቅም። ስሌቱ ሁሌም ዙፋኑ ናት። ዛሬ ሰውዬው ስራው ሁሉ ባልበላው ልበትነው እንደሆነ የሚመስክሩት፣ የራሱ ግልገሎች ጭምር ሆነዋል። እርሱ እስካለ ድረስ ደግሞ ሰላም አይኖርምና (ስልጣን ላይ የማቆያ ቀዳሚ ስትራቴጂው ጦርነትና ስርዓት አልበኝነትን ማንገስ ሆኗልና) ቀዳሚው ትኩረት፣ እርሱን በግዜያዊ የባላደራ ወይም የሽግግር መንግስት መተካት ነው መሆን ያለበት። ይህን ለማድረግ ደግሞ ደም በተቃቡት፣ በማይግባቡት፣ በሚናቆሩት፣ እና እርስ በእርስ በጎሪጥ በሚተያዩት መካከል መነጋገርና መወያየት መጀመር ያስፈልጋል።

6. ወደ ሽግግሩ ለማቅናትም ሆነ ከሽግግሩ ብኋላ መደበኛ መንግስት ለማቋቋም፣ ሁሉም በህገ-ልቦና መገዛት ይኖርብታል። ብልጣብልጥነት አራዳነት ለሚመስለው ማህበረሰ ይህ ከባድ ቢመስልም፤ ሰላም ከተፈለገ ታዳጊ ህጻናት ሳይቀሩ የሚያውቁትን ይህን መሰረታዊ መርህ ለመተግበር ቁርጠኝነት ወሳኝ ነው፥ “በራስ ላይ እንዲደርስ እማትሻውን ነገር በሌሎች ላይ ከማድረግ ከተቆጠብክ” በሰላም የማትኖርበት ምንም ምክንያት አይኖርም። የኮንሰንሰስ ቤዝድ ዴሞክራሲ መሰረቱም ይኸው ነው። የብልጣብልጥ መንገድ መጨረሻው ምን እንደሆነ ባለፉት አምስት አመታት ሁሉም አይቶታል። ማንም አልተጠቀመም። ተያይዞ እንጦሮጦስ ወረደ እንጂ።  ከቅርብ ታሪካችን መማር ከቻለ የመትረፍ ተስፋ ይኖራል።

7. አልወያየም፣ አልነጋገርም፣ አልደራደርም፤ ፍላጎቴን በጉልበትና በዘዴ አሳካለሁ፣ ወዘተ… ብትል ያው ተሽመድምደህ ትቀራለህ። ሰውዬውና ዙፋኑ እንደሙጫ ተጣብቅውልህ ይቆያሉ።

አመቱ ከመገባደዱ በፊት፣ ልተንፍሳትና እናስብበት ብዬ ነው።

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

March 31, 2026

ጽምዶ

March 28, 2026

ክሪቶ በፕላቶ

February 18, 2026

ፍራንከንስታይን፥ አዲስ መፅሓፍ በገበያ ላይ!

September 11, 2025

My Replication Codes Project Gains Wider Recognition

September 12, 2020

Replication Codes for Popular Econometrics Books – All Examples

April 28, 2020

Econometric Analysis of Cross Section and Panel Data with STATA R and PYTHON

Popular
  • From Oslo to The Hague – The journey of Abiy Ahmed...November 7, 2020 - 3:06 pm
  • Reads Atlas Shrugged
    My top reads of 2023December 31, 2023 - 3:40 pm
  • የትግራይ ህዝብ እና የህውሓት ግኑኝነት...September 29, 2016 - 12:30 am
  • ጸበባን ቃልሲን ህዝቢ ትግራይ ከመይ...January 26, 2021 - 1:36 pm
  • ከምጽዓተ ኢትዮጵያ እንተርፍ ይሆን?...December 29, 2023 - 7:29 pm
  • Wooldridge chapter 4 – ExamplesJanuary 6, 2019 - 11:30 pm
  • IPIS Briefing March 2021 – Ethiopia-Tigray ConflictApril 10, 2021 - 7:03 pm
  • Spatial Mapping of Education DataDecember 24, 2018 - 12:01 am
  • ሶስቱ የጥፋት ፈረሶችና የኢትዮጵያ...November 12, 2020 - 5:48 pm
  • ትርጉም የለሽ ምጥ የለም!November 30, 2020 - 8:35 pm
  • መንግስት እና የህዝብ አስተዳደር –...March 5, 2017 - 2:19 am
  • በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች የሚታዩ...February 8, 2019 - 3:23 pm
Recent
  • ጽምዶMarch 31, 2026 - 8:18 pm
  • ክሪቶ በፕላቶMarch 28, 2026 - 11:37 pm
  • ፍራንከንስታይን፥ አዲስ መፅሓፍ በገበያ...February 18, 2026 - 6:15 pm
  • My Top Reads of 2025December 15, 2025 - 4:31 pm
  • ሓንሳዕ ንደማመፅ እሞ!!October 18, 2025 - 6:16 pm
  • Great Ideas E04. Liberation, Then ReflectionOctober 10, 2025 - 6:54 pm
  • Great Ideas E03 – The Median Isn’t the MessageOctober 3, 2025 - 3:16 pm
  • ሃቅ ሃቁን ብቻ እናውራ ከተባለ ̷...October 1, 2025 - 11:55 pm
  • Great Ideas E02 – Great Scientific Ideas That Changed...September 26, 2025 - 1:30 pm
  • Great Ideas E01 – I, PencilSeptember 20, 2025 - 2:53 pm
  • My Replication Codes Project Gains Wider RecognitionSeptember 11, 2025 - 7:02 pm
  • Free GIS & Remote‑Sensing Toolkit 🌍April 18, 2025 - 9:18 pm
Comments
  • NATNAEL ENDALAMAW DERSHEየገብረህወት ባይከዳኝ መጥሃፍ መንግስት...November 20, 2025 - 5:40 pm by NATNAEL ENDALAMAW DERSHE
  • ሙለርትኽክል አለኻ ፀላኢኻን ፈታዊኻን ፈሊኻ...October 19, 2025 - 8:06 am by ሙለር
  • AwetThis is a very reflective essay about Tigray’s political...October 18, 2025 - 9:13 pm by Awet
  • Solomonሰላም ደረጀ ጽሁፉን እንዴት ማግኘት...April 19, 2025 - 8:32 pm by Solomon
  • ደረጀሶል የዶ/ር ተወልደ አርቲክል በሶፍት...April 19, 2025 - 7:35 pm by ደረጀ
  • Solomonእንኳዕ ሓቢሩ አብጽሓና!January 2, 2024 - 3:13 pm by Solomon
  • Solomonእንኳን አብሮ አደረሰን Babi!January 2, 2024 - 3:13 pm by Solomon
  • SolomonThank you Chombe, I wish you the same!January 2, 2024 - 3:12 pm by Solomon
  • Solomonአሰስ ብትል አንዳንዶቹን ኦንላይን...January 2, 2024 - 3:11 pm by Solomon
  • Brehaneእንኳዕ አብፅሓካ ሰሌ!January 2, 2024 - 2:46 am by Brehane
  • Babiሶል እንኳን አደረሰህ!January 1, 2024 - 7:34 am by Babi
  • ChombeThank you! All the best for 2024!December 31, 2023 - 9:03 pm by Chombe
©2026 - Solomon Negash
  • Home
  • Cons.Book
  • EthioData
  • Feeds
  • Contact
Link to: የአሰብ ጦርነት አይቀሬነት Link to: የአሰብ ጦርነት አይቀሬነት የአሰብ ጦርነት አይቀሬነት Link to: Escaping from the cycle of civil-war and mass violence Link to: Escaping from the cycle of civil-war and mass violence Escaping from the cycle of civil-war and mass violence
Scroll to top Scroll to top Scroll to top