የአሜሪካ ኤምባሲ በኦሮሚያ-ሶማሌ ድንበር የተከሰተውን የጎሳ ግጭት አስመልክቶ ያወጣው መግለጫ
አዲስ አበባ፤ መስከረም 9፤ 2010 ዓ.ም. – በኦሮሚያ እና ሶማሌ አዋሳኝ አካባቢዎች በተለይም በሐረርጌ የጎሳ ግጭትን እና የበርካታ ሰዎችን መፈናቀል አስመልክቶ በሚወጡ አሳሳቢ ዘገባዎች ተረብሸናል፤ ምንም እንኳ ዘገባዎቹ ስለሁኔታው ዝርዝር መረጃ ስለማቅረባቸው ግልጽ ባይሆንም፡፡
በመሆኑም የኢትዮጵያ መንግሥት ግጭቱን ግልጽ በሆነ አካሄድ እንዲያጣራ እና አጥፊዎችን ተጠያቂ እንዲያደርግ እንጠይቃለን፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ፤ ግጭቱ በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚኖሩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለችግሩ ሰላማዊ መፍትሔ እንዲሹ መበረታታት ይኖርባቸዋል፡፡
ኢትዮጵያ ጠንካራ፤ የበለጸገች እና ዴሞክራሲያዊት ሀገር መሆን የምትችለው፤ ግልጽና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ውይይት፤ ግልጽ የመንግሥት አሰራር፤ እንዲሁም የዴሞክራሲ እና የፍትህ ተቋማትን ማጠናከር ስትችል እንደሆነ እናምናለን (ሰረዝ የተጨመረ)።የሰሞኑ ሁነቶች በተጠቀሱ ዘርፎች ይበልጥ ፈጣን እና ተጨባጭ ለውጥ አስፈላጊ እንደሆነ አመላካች ናቸው፡፡
[fbcomments]
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!