የትግራይ ህዝብ እና የህውሓት ግኑኝነት ነባራዊ ገፅታ

መግቢያ

የትግራይ ህዝብ እና የህውሓት ግኑኝነት በተመለከተ በተለያዩ ሰዎች የሚሰነዘሩ አስተያየቶች እስከዛሬ ድረስ አወዛጋቢ ሆነው ቀጥለዋል። እስከዛሬ ድረስ አወዛጋቢ መሆኑ በራሱ በጣም የሚያሳዝንና የሚያሳስብ ነገር ነው። ከዚህ ቀደም በርካታ ሰዎች ለጉዳይ ትኩረት ሰጥተው የጻፉ፡ የሚድያ ሽፋን የሰጡ፡ የግል ምስክርነታቸውንና ግንዛቤያቸውን በተለያየ መንገድ የገለጹ ቢሆንም፡ ወቅቱ የሚጠይቀው ርዕሰ ጉዳይ በመሆኑ እኔም የራሴን እይታ ማስቀመጥ እንዳለብኝ በማመን ይህን ጽሁፍ አዘጋጅቻለሁ። ጽሁፉ ምናልባትም ከዚህ ቀደም ያልነበራችሁን ግንዛቤ እንደሚያስጨብጣችሁ ተስፋ አደርጋለሁ። Read more

ምን በጀን? በወቅታዊ ጉዳይ ላይ የቀረበ አስተያየት

ታላቁ ንቅናቄና የህውሓት ግብረመልስ

በኔ እምነት የኢትዮጵያውያን የነጻነት ንቅናቄ እማይቀለበስ ደረጃ ላይ ደርሷል። ከዚህ ብኋላ መሰረታዊ የስርዓት ለውጥ ሳይመጣ ህዝቡ ከንቅናቄው ያፈገፍጋል የሚል እምነት የለኝም። ለዚህም ነው ታላቁ ንቅናቄ ለማለት የደፈርኩት። በሌላ በኩል ደግሞ ላለፉት 25 ዓመታት ካየነውና ከራሳቸው አንደበት ከሰማነው፡ ህውሓት ስልጣኑን በዚህ መንገድ በቀላሉ ይለቃል ብዬ አላምንም። ዛሬም ድረስ በነ ዓይጋ ፎረምና ትግራይ ኦን ላይን ላይ የምናነባቸው ነገሮች “እኛ ካልመራን አገሪቱ ትበታተን” የሚል እንድምታ ያላቸው ጽሁፎችን ነው። ይህም የሚያሳየው የፖለቲካ የበላይነቱን እንደተቆናጠጡ በስልጣን ላይ ለመቆየት አሉ የተባሉትን አማራጮች በሙሉ አሟጠው እስከመጠቀም ድረስ ሊዘልቁ እንደሚችሉ እንጂ ለህዝብ ጥያቄ ጆሮ አይሰጡም። Read more

የኢትዮጵያ ጉዞ ወዴት? የኋላው ከሌለ የለም የፊቱ! (ክፍል 1)

  • የኢትዮጵያ ፖለቲካዊና ኢኮኖሚያዊ ተቋማት (institutions) በአንድ ወቅት ከአውሮፓ አገራት ጋር ተመሳሳይ ነበሩ። ኢትዮጵያ ከአውሮፓ አገራት ጋር ተነፃፃሪ ቦታ ላይ ነበረች።
  • በመቶዎች የሚቆጠሩ ማንነቶች ከስመው ጥቂት ወጥ የሆኑ ማህበረሰቦች ብቻ ዘመናዊቷን አውሮፓ መስረተዋል። አሁንም ግስጋሴው ወደ አንድነት ነው።
  • አውሮፓ የተከተለችው መንገድ ሌሎች በርካታ አገራት ተከትለውታል። ወይም ቀድመው ሄደውበታል (ለምሳሌ ቻይና)።  ኢትዬጵያ ይህን መንገድ አልተከተለችም። ለምን?
  • የኢትዮጵያ የተለየ መንገድ እንድምታው ምንድን ነው? እነዚህንና ሌሎች ነጥቦችን የሚዳስስ ጽሁፍ በሁለት ክፍል ተዘጋጅቷል። ክፍል አንድ እንሆ። መልካም ንባብ!

Read more