, , , ,

የትግራይ ህዝብ እና የህውሓት ግኑኝነት ነባራዊ ገፅታ

መግቢያ

የትግራይ ህዝብ እና የህውሓት ግኑኝነት በተመለከተ በተለያዩ ሰዎች የሚሰነዘሩ አስተያየቶች እስከዛሬ ድረስ አወዛጋቢ ሆነው ቀጥለዋል። እስከዛሬ ድረስ አወዛጋቢ መሆኑ በራሱ በጣም የሚያሳዝንና የሚያሳስብ ነገር ነው። ከዚህ ቀደም በርካታ ሰዎች ለጉዳይ ትኩረት ሰጥተው የጻፉ፡ የሚድያ ሽፋን የሰጡ፡ የግል ምስክርነታቸውንና ግንዛቤያቸውን በተለያየ መንገድ የገለጹ ቢሆንም፡ ወቅቱ የሚጠይቀው ርዕሰ ጉዳይ በመሆኑ እኔም የራሴን እይታ ማስቀመጥ እንዳለብኝ በማመን ይህን ጽሁፍ አዘጋጅቻለሁ። ጽሁፉ ምናልባትም ከዚህ ቀደም ያልነበራችሁን ግንዛቤ እንደሚያስጨብጣችሁ ተስፋ አደርጋለሁ።

ቅድመ እይታ

በአንድ በኩል ህውሓት ደጋግሞ “እኔና የትግራይ ህዝብ የማንነጣጠል አንድ አካል ነን” የሚል ፕሮፓጋንዳ ሲነዛ ይታያል። በሌላ በኩል ደግሞ ከህዝቡ መካከል በግልጽ “የለም እኛና እናንተ ለየቅል ነን፡ ገዢና ተገዢ ወይም ጨቋኝና ተጨቋኝ ነን” የሚላቸው በጣም ጥቂት ነው። ጥቂት በመሆኑ የተነሳ እና በህውሓት የረዥም ጊዜ የፕሮፓጋንዳ ስራ የተነሳ፣ በአብዛኛው ሌላው ኢትዮጵያዊ ዘንድ ፕሮፓጋንዳው ተቀባይነትን አግኝቶ ቆይቷል። ህዝቡና ድርጅቱ የማይነጣጠሉ ናቸው ተብሎ ተደምድሟል።
“ህውሓት እኔና የትግራይ ህዝብ አንድ ነን ይላል፡ አይደለንም ብሎ የሚከራከር ሰው አልተገኘም። ስለዚህ እነሱ አንድ ነን ካሉ እኛ እንዴት አንድ አይደላችሁም ልንል እንችላለን” ተብሎ ለሚነሳ ጥያቄ አጥጋቢ ምላሽ ለመስጠት አስቸጋሪ ሁኔታ ነበረ። በተጨማሪም “የትግራይ ህዝብ ከሌላው በተለየ በዚህ ስርዓት ተጠቃሚ ነው፣ ከዚህ የተሻለ ሌላ ሊጠቅመው የሚችል ስርዓት አይኖርም፣ ስለዚህ ጥቅሙን ለማስከበር ከስርዓቱ ጎን የግድ ይሰለፋል” ብለው የሚከራከሩም ጥቂት አይደሉም።

የትግራይ

የትግራይ ህዝብ ልዩ ተጠቃሚነት i

በሌላ በኩል ደግሞ “ህዝቡ ህውሓት እኛን አይወክልም ብሎ ለመናገር ያልቻለው ከሌላው በተለየ በትግራይ አፈናው ስለሚያይል ነው።” እንዲህውም “ህዝቡ በተለየ ተጠቃሚ ሊሆን ቀርቶ ከሌላው በባሰ የባርነትና የድህነት ህይወት ውስጥ እየኖረ ነው።” ብለው ምስክርነታቸውን የሚሰጡ ቁጥራቸው የማይናቅ ነው። የዛሬ ዓመት ትግራይን እንዲጎበኙ የተደረጉ አርቲስቶች አብዛኞቹ ራሳቸውን ከዚህ ጎራ መድበዋል። እነ አትሌት ፈይሳ፣ ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፣ ፕ/ር ብርሀኑ ነጋ እና ለሌችም የትግራይ ህዝብ የሚኖረው እንደማንኛው ኢትዮጵያዊ ነው በሚል አቋማቸው እናውቃቸዋለን። እኔም ራሴን ከዚህ ጎራ እመድባለሁ። ክልሉ ውስጥ እንዳደገ፣ እንደተማረና እንደሰራ ሰው ነባራዊውን ሁኔታ ኖሬበት የማውቀው ነውና ይህን አቋም ብይዝ የሚገርም አይሆንም። ማስረዳት ግን ይጠበቅብኛል። እንሆ፥

5 replies
 1. Simon
  Simon says:

  እጅግ በጣም ገራሚ ትንተና ነዉ ሶሎሞን ያቀረብከዉ!!! እዉነታዉን ከነ ሙሉ ጭብጦቹ ስላቀረብከዉ በጣም ልትመሰገን ይገባል!!!

  Reply
 2. kedir Seid Mohammed
  kedir Seid Mohammed says:

  እንደኔ እምነት ይህ ጽሁፍ የትግራይ ህዝብ ያለበትን ተጨባጭ በጥልቀት የመረመረ፤ ምናልባትም ስለ ትግራይና ስለ ህዝቧ አስመልክቶ እስካሁን ካነበብናቸው ጽሁፎች በይዘትም በአቀራረብም የተለየ እንደሆነ አምናለው እናም ካለው ነባራዊ ሁኔታ ተነስቼም እውነት የትግራይ ህዝብ ምን ሁኔታ ላይ ነው ያለው፤ ከሌላው ማህበረሰብ ለየት ያለ የስርአቱ ታማኝ ደጋፊ እንዲሆን ያስቻለው፤ ሰጥ ለጥ ብሎ እንዲገዛላቸው ያደረገው እውነት ወዶ በፍቃዱ ነው ወይስ ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ሰይጣን አይነት ነገር ሆኖበት ነው እናም የመሳሰሉ የብዙ ሰዎች ጥያቄ እዚህ ጽሁፍ ውስጥ መልስ እንደሚገኝባቸው አምናለው። ምናልባትም ያለንን የተሳሳተ እይታ ያስተካክላል ብየ ተስፋ አደርጋለው። ብዙዎቻችን ያለን አመለካከት ላይ ላይ ከሚታዩት አንድአንድ ማኒፈስቴሽኖች የዘለለ በጉዳዩ ላይ ጠለቅ ያለ ግንዛቤ ያለን መስሎ አይሰማኝም።

  መልካም ንባብ ፡)

  Reply

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *