የኢትዮጵያ ፍጻሜ: ጉዞ ወደ ዩጎዝላቪያ?
ኦህዴድ-ብልጽግና፣ መሬት አስመላሹ ብአዴንና ህግደፍ-ሻዕቢያ፣ ህወሓትን ለየብቻ መግጠም ስለማይችሉ፣ ተቧድነው ገጠሙት። ሁሉም የጋራ ጠላት እንጂ የሚያስተሳስራቸው የጋራ ሌላ አጀንዳ የላቸውም። ያሸነፉ በመሰላቸው ማግስት፣ እርስ በእርስ መባላት እንደሚጀምሩ ሳይታለም የተፈታ ነበር። ብዙ ዝርዝር ጽፌያለሁ ስለዚህ ጉዳይ፣ ወደዛ አልመልሳችሁም። ፈትቶ የለቀቀው የአማራ ምልሻ / ልዩ ሀይል የአብይ አሕመድ ዋነኛ ራስ ምታቱ ነው። ይህ ሀይል ለ30 ዓመታት ሲፎክርና ሲሸልል ኖረ እንጂ ተኩሶ አያውቅም። አሁን ተደራጅቶ በቆመህ ጠብቀኝ የመተኮስ እድሉን አገኝቷል። ወልቃይትና ራያን እንዲይዝ ተፈቀደሎታል። ይህ የልብ ልብ ይሰጠውና ፊቱን ወደ ሌላ መሬት የማስመለስ ዘመቻ ያዞራል አልነ። እንሆ፣ በቤንሻንጉል ጉምዝ ልዩ ሀይልና ምልሻውን አሰማርቶ፣ ሲቪሎቹን ለፖለቲካ ትርፍ እየማገደ፣ በሰው ክልል ጦርነት ከፈተ። ኦህዴድና ኦነግም ከጉምዝ ጎን ቆመው እየከተከቱት ይገኛሉ። በጅምላ ተጨፍጭፈው፣ በጭነት መኪና ሬሳቸው እየተነዳ፣ በጅምላ እየተቀበሩ ነው። ሰው ያልዘራውን አያጭድም።
አብይ አሕመድ ያለ የሌለ ጉልበቱን ትግራይ ላይ ጨርሷል። በሌላ ክልል ጸጥታ ሊያስከብር ቀርቶ፣ በትግራይ የጀመረውን መቋጨት አይችልም። ሻዕቢያም ከቁጥጥሩ ውጭ ሆኖ፣ መከላከያ ፈለገ አልፈለገ፤ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደረ ፈቀደ አልፈቀደ፣ ግድ ሳይሰጠው፣ ያሻውን እያደረገ ነው። ይህ ብልጽግናን ከፈሎታል። መከላከያን ከፈሎታል። በመከላከያና በብልጽግና ቅራኔ ፈጠሯል። አሁን ትግራይ መቀበሪያቸው ብቻ ሳትሆን፣ እርስ በእርስ የሚጫረሱባት የጦርነት አውድም እየሆነች ነው።
የአገር ውስጥ ራስ ምታቱ በቤንሻንጉል ጉምዝና በትግራይ ብቻ አይደለም እየታየ ያለው። በኦሮሚያ ኦነግ ግማሹን ቦታ ተቆጣጥሮታል። የኦህዴድ ተከታዮች ሳይቀሩ፣ ወደ ኦነግ ማዘንበል መርጠዋል። ጃል መሮን የሚከተል ሰራዊት፣ በ10ሺዎች የሚቆጠሩ ሆነዋል። በሺዎች የሚቆጠሩ የኦሮሚያ ክልል ያሰለጠናቸው ምልሻዎች፣ ጃል መሮን እየተቀላቀሉ ነው። ድፍን ኦሮሞ “እስከዛሬ ለኢዮጵያ የሞትነው ይበቃል፣ ለአገሪቱ እየሞትን በአገሪቱ እየተከዳንና እየተገደልን መኖር የለብንም፣ ከእንግዲህ ትግላችን ለነጻነታችን መሆን አለበት” ብሏል። አብይ አሕመድ ለስልጣኑ ሲል፣ ኦሮሞን ክዶ፣ ከሁሉም ተነጥሎ ብቻዉን ቀርቶ፣ የነፍጠኛ ስርዓት ለመመለስና ለማንገስ እያሸረገደ ነው ብሎ የሚከሰው ድፍን ኦሮሞ ነው። ብንፈልግ እንኳን ኢዮጵያ ከእንግዲህ የመትረፍ እድል የላትም በማለት ኦሮሞ የራሱን ህልውና ወደሚያስከብርበት፣ ጥቅሙን ወደሚያስጠብቅበት ትግል አቅንቷል።
በሌላ በኩል ደግሞ ቅርቃር ውስጥ እንደገባ የተረዳው አብይ አሕመድ፣ የአማራ ልዩ ሀይልና ምልሻን በማስቀጥቀጥ፣ ነፍጠኛን ለመስበር በማሴር፣ ሱዳን ጦሯን ድንበር ላይ እንድታሰፍር ከሱዳን ጋር መስማማቱን በየሚዳው እየተነገረ ነው። ይህን ሊያደርግ እንደሚችል ከዴይ ዋን ጀምሮ ገምተን ነበር። የልብ ልብ የሰጠው ነፍጠኛ ከሱዳን ጋርም ይተናኮሳል፣ ቢተናኮስም በአብይ ትዕዛዝ ከመከላከያ ድጋፍ አያገኝም የሚል መላምት አስቀምጠን ነበር። እንደተገመተው ብቻ ሳይሆን ከገመትነው ባላይ ነው እየሆነ ያለው። ራሱ አብይ፣ ጦርነቱን የጀመሩትን የአማራ ምልሻና ልዩ ሀይል በይፋ በማህበራዊ ሚድያ ገጾቹ ኮንኗል። የኛን ሰላም የማይሹና የሁለቱ አገራት ወዳጅነት የማይረዱ ናቸው፣ ሲል በሱዳን ወታደር ክፉኛ መቀጥቀጣቸው ሳያንስ ድርጊታቸውን ኮንኗል። ከዛ ብኋላ ነው መከላከያ ለሁለት የተከፈለው። ከአብይ ትዕዛዝ ውጭና ከብርሃኑ ጁላ እውቀት ውጪ፣ በነፍጠኛው የሚመራ የመከላከያ ብራንች ከሱዳን ጋር መጠነኛ ጦርነት ከፍቶ ቆይቷል። አሁንም እንደተፋጠጠ ነው። ምልሻው ብቻዉን ስላልቻለ፣ ጦርነቱን በሁለት ሉአላዊ አገራት መካከል ለማድረግና ከሌላው ህዝብ የድረሱልኝ ጥሪ ለማሰማት ነው ትንኮሳው። በዚህ የብልጽግና መሪዎች አልተስማሙም። ለበርካታ ቀናት አብይ አሕመድ የገባበት አይታወቅም። አንዴ ተመርዟል፣ ሌላ ጊዜ ታሟል፣ ሌላ ጊዜ ታፍኗል የሚል ወሬ እንደሰማን አለን። ምንም ይሁን ምን፣ አገሪቱን አክቲቭሊ እየመራ እንዳልሆነና ለበርካታ ቀናት ከህዝብ እየታ ርቆ እንዳለ ግልጽ ነው።
ይህ ሁሉ ሔዶ ሔዶ የሚጠናቀቀው በአንድ አስቀያሚ እልቂት ነው። በተለይ በኦሮሚያና በአማራ ክልል የሰለጠኑ ልዩ ሀይሎች፣ እርስ በእርስ የሚጫረሱበት ግዜ እየመጣ ነው። ፊንፊኔ/አዲስ አበባ እየተሰማ ያለው ተኩስና ፍንዳታ፣ እየታየ ያለው የእሳት ቃጠሎ፣ የፍጻሜው መነሻ ምልክቶች ናቸው። ኢዮጵያ ከሞተችና ከተበተነች ሰነባብታለች። ክፋቱ በሰላም መለያየት ሲቻል፣ በደም አፋሳሽ መንገድ እንዲሆን፣ መንጋው መምረጡ ነው ጉዞዋን ወደ ዩጎዝላቪያ እየቃኘ ያለው።
የህወሓት መሪዎችን በማሰርና በመግደል የተወሳሰበና ለክፍለዘመናት የኖረ ችግራቸውን የሚፈቱ መስሏቸው የነበሩ ሰዎች ዛሬ፣ ትግራይ ላይ ቃታቸውን የሳቡባትን ቀን መርገም ጀምረዋል። ገና ነው፣ ጸጸቱ የምትችሉት አይሆንም።
Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!