የኖርዌዩ ልዑል ሆኮን በህዳር ወር ኢትዮጵያን እንደሚጎበኝ ተገለፀ


ልዑል ሆኮን ከባለቤታቸው ልዕልት መተ-ማሪት ጋር በመሆን በህዳር ወር ለሶስት ቀናት ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ አንደሚያቀኑ ተገለፀ።

የኖርዌጅያን ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስሪያ ቤት ትላንት ለጋዜጦች በሰጠው መግለጫ፣ ልዑል ሆኮን ከህዳር 7 እስከ ህዳር 9 ድረስ የሚዘልቅ ኦፊሴላዊ የሶስት ቀናት ጉብኝት በኢትዮጵያ ለማድረግ ቀጠሮ መያዛቸውን ገለጿል።

በሶስት ቀናት ቆይታቸውም ጤና፣ ትምህርት፣ አየር ለውጥና ስደት ከአበይት የመወያያ አጀንዳቸው መካከል እንደሚገኙበት ተጠቁሟል። ኖርዌይ ከኢትዮጵያ በትብብር ከምትሰራባቸውቸው መስኮች መካከል የአየር ጠባይ ለውጥና የአቅም ግንባታ እንደሚገኙበት ይታወቃል። ባለፈው ወር ኖርዌይ ለአካባቢና ደን ጥበቃ የ600 ሚልዮን ኖርዌጅያን ክሮነር (~80 ሚልዮን ዶላር) ድጋፍ ለኢትዮጵያ መስጠቷም ይታወቃል።

ኖርዌይ ከአፍሪካ ህብረት ጋር ያላት ትብብር በተመለከተም ልዑሉ ከሚመለከታቸው ጋር ለመወያየት በአጀንዳቸው ማካተታቸውን ተጠቁሟል።

ልዑል ሆኮን በሶስት ቀናት ቆይታቸው ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት, የሲቪል ማህበረሰብ, የኖርዌይ ተቋማት እና የንግድ ተወካዮች ተገናኝተው ይነጋግራሉ ተብሎ ይጠበቃል።


ምንጭitromso.no & regjeringen.no

[fbcomments]

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *