አዲሱ መጽሐፌ ፍራንከንስታይን አሁን በገበያ ላይ!
BySolomon|February 18, 2026
እ.ኤ.አ. በ1818 በሜሪ ሼሊ ተጽፎ በዓለም የሥነ-ጽሑፍ ታሪክ ከፍተኛ ዝናን እና ተወዳጅነትን ያተረፈው “ፍራንከንስታይን” (Frankenstein; or, The Modern Prometheus) እነሆ ለመጀመሪያ ጊዜ በአማርኛ ተተርጉሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ በዲጂታል አማራጮች ለንባብ በቅቷል።
መጽሐፉ ሳይንሳዊ ልብ-ወለድንና ጥልቅ ፍልስፍናን አጣምሮ የያዘ ሲሆን፣ የሰው ልጅ ሕይወትን ለመፍጠር ስላደረገው ጥረትና ያ አስደናቂ ሙከራ ስላስከተለው መዘዝ በአስፈሪ ሁኔታ ይተርካል። ዶክተር ቪክቶር ፍራንከንስታይን የፈጠረው “ፍጥረት” ማንነቱን ፍለጋ በሚያደርገው ጉዞ የደረሰበትን መገለል በሚያሳዝንና በሚያስፈራ ሁኔታ ያቀርባል።
ይህን ዘመን ተሻጋሪ ሥራ ባሉበት ሆነው በስልክዎ ወይም በታብሌትዎ በቀላሉ ለማንበብ ከታች ያሉትን ሊንኮች ይጎብኙ፦


አማርኛEnglish

Leave a Reply
Want to join the discussion?Feel free to contribute!