“ምጣኔ ፍቅር”

… ልጁ ከፍቅረኛው ጋር ትንሽ እክል ገጠመው። በቃ 16 ሰዓት በቀን ስራ ላይ ናቸው። ስንት ቢል አለ። አገር ቤት ስንት እጁን ዘርግቶ የሚጠባበቅ ቤተሰብ አለ። እና ከዛ ቢዚ ቀን ቤት ገብተው ምግብ ማን ያብስል? ዲሾቹን ማን ይጠባቸው? ቆሻሻውን ማን ይድፋ? አልጋውን ማን ያንጥፍ? ቤቱን ማን ያጽዳ? ልብሶቹን ማን ይጠብ (ማሽን ለሚያጥበው)? ማን ሾፕ ያድርግ? ሁሌ በቃ ትንሽ መነጫነጭ፣ ማማረር ሆነ። ለፍቅር ማለቴ ለፍቅር (አለ አይደል) ጊዜ አጡ። እና ምን ይበጀን ብለው አማካሪዎች ዘንድ ሄዱ።

ባህላዊ መንገድ ሞከሩ። ጤና አዳም የሚመስል ነገር በሻይ እየነከሩ እንዲሞክሩ ተደረገ። ወፍ የለም።
ሳይኮሎጂስቶች ዘንድ ሄዱ። ስጦታ ገዝተው እንዲሰጣጡ አማከረ። ኪሳቸውን ከማራቆቱ ውጪ ምንም አልፈየደም።
ብዙ ቦታ ሞከሩ ለውጥ የለም። ተስፋ በመቁረጥ ልጁ እኔ ዘንድ መጣና ብሶቱን ተነፈሰ። ታድያ እኔ ምን ላድርግ። የተማርኩት ኢኮኖሚክስ፣ ውሎዬ ፖለቲካ፣ ስለ ፍቅር ምኑን አውቄው አልኩት። ጓደኛ ለመቼ ነው ሲል ተማጠነኝ። ተስፋ ላስቆርጠው አልፈለግኩምና እሺ በል ብዬ የሙከራ ጣቢያ አደረኩት …ሄሄ

“እንደሚመስለኝ ፍሬንድ ችግራችሁ የጊዜ ማጣት ነው። ጊዜ ለማብቃቃት ሞክሩ። ማህበራዊ ሚድያ ትጠቀማለህ?” አልኩት።
“እረ በጭራሽ። ዩ ትዩብ ዘፈን አዳምጣለሁ፣ ኢሳት ዜና እሰማለሁ፣ ይኸው ነው።” ሲል መለሰልኝ።

በቃ ወዲያው ገባኝ፣ የሆነ ውለታ እንደምውልለት

“እንደዛ ከሆነ ጥሩ። ቤት እንዴት ነው division of labor የሚባል ነገር አለ ሞክራችሁታል።”

“ማለት?”

“Adam Smith ምን ይላል መሰለህ ሰዎች specialize ባደረጉበት ሙያ መሰረት ስራ ቢከፋፈሉ ውጤታማ ይሆናሉ። ይህን በቤተሰብ ስራ ክፍፍል ውስጥ ብትሞክሩት ትርፉ ጊዜ መቆጠብ ይሆናል። በቆጠባችሁት ጊዜ በጋራ ዘና ትሉበታላችሁ።”

“እቤት ውስጥ የሚሰሩ ስራዎች በሙሉ specialize ያደረገችው እሷ ነች። ያበሻ ወንድ ታውቀዋለህ መቼስ። ምንም ስራ እኮ አንችልም።”

“በAdam Smith አገላለጽ በሁሉም ዘርፍ Absolute Advantage አላት ማለት ነው። ሁሉንም ለሷ ከተውክላት፣ ለፍቅር ቀርቶ ለግልምጫም ጊዜ አይኖራት። Milton Friedman “There is no such a thing called Free Lunch” ያለውን ነገር ማሰብ አለብህ።”

“እና ምን ተሻለን ታድያ”

“እስቲ በዴቪድ ሪካርዶ concept ደግሞ እንሞክር። በየትኛው ዘርፍ comparative advantage አለኝ ብለህ ታስባለህ?”

“ምን ማለት ነው ይሄ ደግሞ”

“ማለቴ፣ ከቤት ውስጥ ስራ የግድ መስራት አለብህ ብትባል የትኛውን ለመስራት ትመርጣለህ፣ የትኛውን በተሻለ ፍጥነት ታከናውናለህ?”

“ከባድ እቃ ማንሳት፣ ቆሻሻ ማስወገድ፣ ልብስ ማጠብ”

“ጎሽ ሌሎችም እንዲህ ጨማምረህ ስራ ተካፈልና በፍጥነት ለመጨረስ ሞክር። እርሷ የምትጨምርህ ስራ ካለም ካንተ የመቀበል ፍላጎት (willingness to accept) ጋር እንዲመጣጠን አድርግ። አየህ ፍቅር በመተሳሰብ (bounded rationality) እንጂ እንደነጻ ገበያ በራስወዳዶች (selfish agents) ፉክክር (compitition) አይሰራም። ይህን ካደረጋችሁ፣ ለleisure ትንሽ ጊዜ save ታደርጋላችሁ። ከዛ በተገኘው አጋጣሚ incentive ተሰጣጡ። የግድ የቁስ መሆን የለበትም። በትክክለኛ ጊዜና ሁኔታ “አመሰግናለሁ ውዴ” ማለትም በራሱ በቂ ነው። ክርክር ላይ risk averse አትሁን። አንዳንዴ እያወቅክም ቢሆን ተሸነፍላት – በሌላ አነጋገር risk taker ሁን። በመካከላችሁ information assymetry እንዳይኖር የመረጃ ሽንቁርህን ቶሎ ቶሎ ድፈን። ውሎህን አካፍላት። ውሏዋን ታካፍልህ። እምነት በጣለችብህ ጉዳይ ላይ moral hazard እንዳትፈጽም ተጠንቀቅ። ስሜቷን አጥና። የምታወራውን ፍላጎት (stated preference) ሳይሆን የምታሳየውን ገስቸር (Revealed Preference) ለመረዳት ሞክር። Revealed Preferenceዋን በደንብ የተረዳህ እለት demand እና supplyን ለማመጣጠን ሞክር። … ”

ይቺን ምክር አፉን ከፍቶ ከሰማ ብኋላ ተለያየን። እንዳጋጣሚ ከወራት ብኋላ መንገድ ላይ ተገናኘን።

“እንዴት ነው ሰራ?” አልኩት። ፊቱ እንደመከስከስ ብሏል።

“ጉድ ሰራኸኝ እኮ” አለኝ

“ምነው?”

“አርግዘናል”

Take it easy  bro, that’s the equilibruim price!

0 replies

Leave a Reply

Want to join the discussion?
Feel free to contribute!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *