ኢትዮጵያ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸውን 3 የበቀሎ ዝሪያዎች በስፋት አምርታ ለገበያ ለማቅረብ ተስማማች
ኢትዮጵያ በፖለቲካ አለመረጋጋት እና በጦርነት እየታመሰች ባለችበት፣ ህዝቡ በኑሮ ውድነት እና ባለው የፖለቲካ ሁኔታ ናላው በዞረበት፣ በአለም ላይ በተለያዩ አቅጣጫው ትኩረቱን የሚናጠቁ ትልልቅ ጉዳዮች ባሉበት በዚህ ሰዓት፣ የኢትዮጵያ መንግስት ለትውልድ የሚተርፍ አጥፊ ፖሊሲዎችን እያስፈጸመ ይገኛል። በዓለም ዓቀፍ የገንዘብ ተቋም ግፊት የተፈጸመው የኢኮኖሚ ሪፎርም ከታሰበለት በተቃራኒ ኢኮኖሚውን አመሰቃቅሎ፣ ምንዛሪው አሁን በብሔራዊ ባንክ ትዕዛዝ ከፍና ዝቅ የሚል ሆኗል። ነጻ ይሆናል የተባለው ሜዳ ከአንድ ሳምንት ሳይዘል መልሶ ታፍኗል፣ እንደበፊቱ በግልጽ ቋንቋ የሚነገር ባይሆንም። ይህ ሪፎርም እያስከተለ ያለው ጦስ አንሶ፣ ባሳለፍነው ወር የኢትዮጵያ መንግስት የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው የበቀሎ ዝሪያዎች በስፋት ለማብቀል መስማማቱን በዓለም ዓቀፍ ሚድያዎች እና መያድ-ኦች ሲዘገብ ሰንብቷል።
These newly introduced varieties are genetically engineered for improved insect resistance and drought tolerance, with the potential to yield up to 60 percent more than conventional maize varieties. By adopting this biotech innovation, TELA maize has become Ethiopia’s first genetically engineered food crop.
ይህንን ውሳኔ በመቃወም የተለያዩ አካላት (ግለሰቦች እና ድርጅቶች) የተቃውሞ ፊርማ ሲያሰባስቡ ሰንብተዋል። በዚህ መግለጫቸው ላይ እንዳሳወቁት የኮርፖሬቶችን ጥቅም የሚያስጠብቅ እና በህዝብ ላይ ሊያደርስ የሚችለውን ጥፋት ያላገናዘበ መሆኑን አመላክተዋል።
GMOs are pushed in Ethiopia by corporate interests in the absence of rigorous, independent impact assessments and proper biosafety protocols. … The institutions that are set up to protect us from risks arising out of the planting and use of GMOs are not equipped to protect the health of the people and the environment. The institution that is responsible to ensure the implementation of the Biosafety Proclamation (No. 896/2015) … is understaffed and has low political clout to protect the interest of citizens.
ይህ በእንዲህ እንዳለ ከብዙ ክርክር ብኋላ አውሮፓም ለዘረመል ልውጥ ዘሮች እጇን በተወሰነ ደረጃ እየሰጠች ትገኛለች። ከሁለት አመት በፊት፣ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው 3 የበቀሎ ዝሪያዎች ለእንስሳት መኖነት ብቻ እንዲውሉ ፈቅዳ የነበረ ሲሆን፣ ዘንድሮ ደግሞ ለምግብነት መዋል የሚችሉ መሆናቸውን ተቀብላለች። ነገር ግን አሁንም እነዚህን የበቆሎ ዝርያዎች ጨምሮ ማንኛውም የዘረመል ለውጥ የተደረገበት እህል በአውሮፓ ምድር ላይ ማብቀል የታገደ መሆኑን በጽኑ አሳውቃለች። ሌሎች አገራት አምርተው ወደ አውሮፓ አገራት ኤክስፖርት ማድረግ ይችላሉ ማለት ነው። ታድያ ምርቶቹ የዘረመል ለውጥ የተደረገባቸው መሆኑን በግልጽ የሚያሳይ ሌበል ሊኖራቸው ይገባል። ይህም ሸማቹ የሚገዛውን እህል በደንብ አውቆ ነው የሚገዛው። ታድያ እነዚህ ምርቶች (ምርታማነታቸውን ለመጨመርም ስለሆነ የዘር ምህንድስና የሚደረግባቸው) ከጤነኛውና ኦርጋኒኩ ምርት በተለየ መልኩ እጅግ የረከሱ ስለሚሆኑ፣ በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሰዎች (በአብዛኛው ኢምግራንቶች) የሚመገቡት ነው ሊሆን የሚችለው። ዞሮ ዞሮ ስደተኛው፣ በአገሩም ከአውሮፓም ውስጥ እንደ ጊኒፒግ የሙከራ ጣቢያ ሆኖ ያገለግላል።
ዋቢ ማጣቀሻዎች፡
ሶል የዶ/ር ተወልደ አርቲክል በሶፍት ኮፒ እንዴት ማግኘት ይቻላል? እባክህን ኮፒው ካለህ ከላይ ባስቀመጥኩት ኢሜይል አድሬስ ላክልኝ።
ሰላም ደረጀ ጽሁፉን እንዴት ማግኘት እንደምትችል ኤሜይልድ አድርጌልሃለሁ። መልካም ንባብ!